የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ሕዝቤን አጽናኑ”
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 28, 29. (ሀ) ይሖዋ ደካሞችን እንደሚረዳ ሕዝቡን ያሳሰባቸው እንዴት ነው? (ለ) ይሖዋ ለሕዝቡ ኃይል የሚሰጠው እንዴት እንደሆነ ለማስረዳት የተጠቀሰው ምሳሌ ምንድን ነው?

      28 ይሖዋ ትካዜ ላይ ለወደቁት ግዞተኞች በኢሳይያስ አማካኝነት ማበረታቻ መስጠቱን ይቀጥላል:- “ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፣ ጉልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፣ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፣ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።”​—⁠ኢሳይያስ 40:​29-31

      29 ይሖዋ ለደከሙት ኃይልን ስለመስጠት ሲናገር ግዞተኞቹ ወደ ትውልድ አገራቸው መመለስ የሚጠይቅባቸውን አስቸጋሪ ጉዞ በአእምሮው ይዞ ሊሆን ይችላል። ይሖዋ ለእርዳታ ወደ እርሱ የሚመጡትን የደከሙ ሰዎች መደገፍ ባሕርይው እንደሆነ ያስታውሳቸዋል። ብርቱ የሚባሉት ሰዎች ማለትም ‘ብላቴኖችና’ ‘ጎበዛዝት’ እንኳ በድካም ሊታክቱና ሊወድቁ ይችላሉ። ይሁንና ይሖዋ በእርሱ ለሚታመኑት ሰዎች ለመሮጥና ለመራመድ የሚያስችላቸውን ኃይል ይሰጣቸዋል። ያለ ፋታ ለሰዓታት ማንዣበብ የሚችለው የንስር ወፍ የሚያደርገው ብዙም ድካም የማይጠይቅ መስሎ የሚታይ በረራ ይሖዋ ለአገልጋዮቹ እንዴት ኃይል እንደሚሰጣቸው በጉልህ የሚያስረዳ ምሳሌ ይሆናል።d አይሁዳውያኑ ግዞተኞች እንዲህ ያለውን መለኮታዊ ድጋፍ የማግኘት ተስፋ ስላላቸው ተስፋ የሚቆርጡበት ምክንያት የለም።

  • “ሕዝቤን አጽናኑ”
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 30. ዛሬ ያሉ እውነተኛ ክርስቲያኖች ከኢሳይያስ ምዕራፍ 40 የመደምደሚያ ቁጥሮች ማጽናኛ ማግኘት የሚችሉት እንዴት ነው?

      30 የ⁠ኢሳይያስ ምዕራፍ 40 የመጨረሻ ቁጥሮች በዚህ ክፉ የነገሮች ሥርዓት የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ለሚኖሩት እውነተኛ ክርስቲያኖች ጥሩ መጽናኛ ይዘዋል። ተስፋ እንድንቆርጥ ሊያደርጉን የሚችሉ ብዙ ተጽእኖዎችና ችግሮች ባሉበት በዚህ ጊዜ በጽናት የምንቋቋማቸውን መከራዎችና የሚደርስብንን የፍትሕ መጓደል አምላክ እንደሚመለከት ማወቃችን የሚያጽናና ነው። ‘ለጥበቡ ቁጥር የሌለው’ የሁሉ ነገር ፈጣሪ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ በራሱ መንገድ የፍትሕ መጓደሉን እንደሚያስተካክለው እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን። (መዝሙር 147:​5, 6) እስከዚያው ድረስም ለመጽናት የምንታገለው ብቻችንን አይደለም። ምንጩ የማይነጥፈው ይሖዋ በፈተና ወቅት ለአገልጋዮቹ ብርታት አልፎ ተርፎም ‘ከወትሮው የበለጠ ኃይል’ ሊሰጣቸው ይችላል።​—⁠2 ቆሮንቶስ 4:​7 NW 

  • “ሕዝቤን አጽናኑ”
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • d ንስር ብዙም ኃይል ሳይጠይቅበት ከፍ ብሎ እየተንሳፈፈ ይቆያል። ይህንን የሚያደርገው ሙቅ አየር ወደ ላይ የሚወጣባቸውን መስመሮች ወይም ቴርማልስ በመከተል ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ