የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አባትና ዓመፀኛ ልጆቹ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 20 ኢሳይያስ ይህንን ትንቢታዊ መልእክት እንደሚከተለው በማለት ይደመድማል:- “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር።” (ኢሳይያስ 1:​9)c ይሖዋ በመጨረሻ ይሁዳን በአሦራውያን ክንድ ከመደቆስ ይታደጋታል። ሰዶምና ገሞራ እንደጠፉት ይሁዳ ሙልጭ ብላ አትጠፋም። በሕይወት ትቀጥላለች።

      21. ባቢሎን ኢየሩሳሌምን ካጠፋች በኋላ ይሖዋ ‘ጥቂት ቀሪዎችን’ የተወው ለምንድን ነው?

      21 ከአንድ መቶ የሚበልጡ ዓመታት ካለፉ በኋላ ይሁዳ እንደገና ሌላ አደጋ አጠላባት። ሕዝቡ በአሦራውያን አማካኝነት ከተሰጠው ተግሳጽ አልተማረም። “እነርሱ ግን . . . በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፣ ቃሉንም ያቃልሉ፣ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።” ከዚህም የተነሣ ‘ፈውስ እስከማይገኝላቸው ድረስ የእግዚአብሔር ቁጣ በእነርሱ ላይ ሆነ።’ (2 ዜና መዋዕል 36:​16) የባቢሎናውያኑ ንጉሠ ነገሥት ናቡከደነፆር ይሁዳን ድል አድርጎ ተቆጣጠራት። በዚህ ጊዜ ግን “በወይን ቦታ እንዳለ ዳስ” ያለ ነገር እንኳ አልቀረላትም። ኢየሩሳሌም ሳትቀር ተደመሰሰች። (2 ዜና መዋዕል 36:​17-21) ያም ሆኖ ይሖዋ ‘ጥቂቶች እንዲተርፉ አድርጓል።’ የይሁዳ ሰዎች 70 ዓመት በግዞት ቢቆዩም ይሖዋ የብሔሩ ሕልውና እንዲቀጥል በተለይ ደግሞ ተስፋ የተሰጠበት መሲህ የሚገኝበት የዳዊት መስመር እንዳይጠፋ አድርጓል።

      22, 23. በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይሖዋ ‘ጥቂት ቀሪዎችን’ የተወው ለምንድን ነው?

      22 እስራኤላውያን በመጀመሪያው መቶ ዘመን የደረሰባቸው መከራ የአምላክ የቃል ኪዳን ሕዝብ ሆነው የተቀበሉት የመጨረሻው መከራ ነበር። ኢየሱስ ተስፋ የተሰጠበት መሲሕ ሆኖ በመጣ ጊዜ ብሔሩ ሊቀበለው ፈቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ይሖዋም እነርሱን ሳይቀበላቸው ቀርቷል። (ማቴዎስ 21:​43፤ 23:​37-39፤ ዮሐንስ 1:​11) ይሖዋ ከዚህ በኋላ በምድር ላይ የተለየ ሕዝብ አይኖረውም ማለት ነውን? በፍጹም። ሐዋርያው ጳውሎስ ኢሳይያስ 1:​9 ሌላ ፍጻሜ እንደሚኖረው ጠቁሟል። ከሰፕቱጀንት ትርጉም በመጥቀስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ኢሳይያስም እንደዚሁ:- ጌታ ፀባዖት ዘር ባላስቀረልን እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር ብሎ አስቀድሞ ተናገረ።”​—⁠ሮሜ 9:​29

      23 በዚህ ወቅት በሕይወት የተረፉት በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑት ቅቡዓን ክርስቲያኖች ናቸው። በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ ያመኑ አይሁዳውያን ነበሩ። በኋላ ግን ያመኑ አሕዛብም ከእነርሱ ጋር ተቀላቅለዋል። አንድ ላይ ‘የእግዚአብሔር እስራኤል’ የተባለውን አዲሱን የእስራኤል ብሔር መሥርተዋል። (ገላትያ 6:​16፤ ሮሜ 2:​29) በ70 እዘአ በአይሁዳውያን የነገሮች ሥርዓት ላይ ከደረሰው ጥፋት የተረፈው ይህ ‘ዘር’ ነው። በእርግጥም ደግሞ ‘የእግዚአብሔር እስራኤል’ ዛሬም ከእኛ ጋር አለ። ዛሬ “አንድ እንኳ ሊቈጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች” ለመሆን የበቁ በሚልዮን የሚቆጠሩ ያመኑ ሰዎች ከብሔራት ተውጣጥተው ከእነርሱ ጋር በመተባበር ላይ ናቸው።​—⁠ራእይ 7:​9

      24. እስከ ዛሬ በሰው ዘር ላይ ከደረሱት ጥፋቶች ሁሉ ከከፋው ጥፋት በሕይወት ለመትረፍ የሚፈልጉ ሰዎች ልብ ሊሉት የሚገባው ነገር ምንድን ነው?

      24 በቅርቡ ይህ ዓለም ከአርማጌዶን ጦርነት ጋር ፊት ለፊት ይፋጠጣል። (ራእይ 16:​14, 16) ይህ አሦራውያንም ሆነ ባቢሎናውያን ይሁዳን መውረራቸው ካደረሰው ጉዳት እንዲሁም በ70 እዘአ ሮማውያን በይሁዳ አውራጃ ላይ ካደረሱት ውድመት እጅግ የሚከፋ ቢሆንም በሕይወት የሚተርፉ ሰዎች ይኖራሉ። (ራእይ 7:​14) እንግዲያውስ ሁላችንም ኢሳይያስ ስለ ይሁዳ የተናገራቸውን ቃላት መመርመራችን ምንኛ አንገብጋቢ ነው! እነዚህ ቃላት በዚያ ዘመን የነበሩትን ሰዎች ሕይወት ለማትረፍ አስችለዋል። ዛሬም ቢሆን የሚያምኑትን ሰዎች ሕይወት ሊያተርፉ ይችላሉ።

  • አባትና ዓመፀኛ ልጆቹ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • c በሲ ኤፍ ካይል እና በኤፍ ዴሊሽ የተዘጋጀው ኮሜንታሪ ኦን ዚ ኦልድ ቴስታመንት እንዲህ ይላል:- “የነቢዩ ንግግር እዚህ ላይ ትንሽ ቆም ብሏል። እዚህ ቦታ ላይ ለሁለት ክፍል መለየቱን የምናውቀው በኢሳይያስ 1 ቁጥር 9 እና 10 መካከል በተተወው ክፍት ቦታ ነው። ክፍት ቦታ በመተው ወይም የተጀመረውን መስመር ድንገት በማቋረጥ ትላልቅም ሆኑ ትናንሽ ክፍሎችን የመለየት ዘዴ የአናባቢ ወይም የአደማመፅ ምልክቶችን ከመጠቀም አንጻር ሲታይ በጣም ጥንታዊ በሆነ ልማድ ላይ የተመሠረተ ነው።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ