-
‘እኔ፣ አምላክህ ይሖዋ፣ ቀኝ እጅህን እይዛለሁ’መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥር 1
-
-
‘እኔ፣ አምላክህ ይሖዋ፣ ቀኝ እጅህን እይዛለሁ’
አንድ አባት ከልጁ ጋር የመኪና መንገድ በሚያቋርጥበት ጊዜ ልጁን “እጄን ያዘኝ” ይለዋል። ልጁ በትንናሽ እጆቹ ሰፊ የሆነውን የአባቱን እጅ ጥብቅ አድርጎ ከያዘ ምንም ነገር አይፈራም። አስተማማኝ ያልሆኑ ነገሮች በሞሉበት በዚህ ዓለም ውስጥ እጅህን ይዞ የሚመራህ እንዲኖር የተመኘህበት ጊዜ አለ? ከሆነ ኢሳይያስ የጻፈው ሐሳብ ሊያጽናናህ ይችላል።—ኢሳይያስ 41:10, 13ን አንብብ።
ኢሳይያስ እነዚህን ቃላት የተናገረው ለእስራኤል ብሔር ነበር። አምላክ እነዚህን ሕዝቦች “የተወደደ ርስቴ” ብሎ ቢጠራቸውም በዙሪያቸው ያሉት ብሔራት ጠላት ሆነውባቸው ነበር። (ዘፀአት 19:5) ታዲያ እስራኤላውያን መፍራት ነበረባቸው? ይሖዋ በኢሳይያስ በመጠቀም የሚያበረታታ መልእክት ልኮላቸዋል። ይህን ሐሳብ በምንመረምርበት ጊዜ ጥቅሱ በዘመናችን ላሉ የይሖዋ አምላኪዎችም እንደሚሠራ እናስታውስ።—ሮም 15:4
-
-
‘እኔ፣ አምላክህ ይሖዋ፣ ቀኝ እጅህን እይዛለሁ’መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥር 1
-
-
ታዲያ የይሖዋ አምላኪዎች ከእሱ ምን መጠበቅ ይችላሉ? ይሖዋ “በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ” በማለት ቃል ገብቷል። (ቁጥር 10) አክሎም “እኔ፣ . . . አምላክህ ይሖዋ፣ ቀኝ እጅህን እይዛለሁ” ብሏል። (ቁጥር 13 NW) እነዚህን ጥቅሶች ስታነብ ወደ አእምሮህ የሚመጣው ምንድን ነው? አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ “እነዚህን ሁለት ጥቅሶች በአንድ ላይ ስናያቸው በወላጅና በልጅ መካከል ያለውን ግንኙነት ጥሩ አድርገው ይገልጻሉ” ይላል። “[አባትየው] ልጁ ችግር ቢያጋጥመው ለመከላከል በማሰብ ቆሞ በመጠበቅ ብቻ አይወሰንም፤ ከዚህ ይልቅ ከልጁ ጋር አብሮ ይሆናል። ልጁ ከእሱ እንዲለይ አይፈቅድም።” እስቲ አስበው፦ ይሖዋ፣ ሕዝቡ ከእሱ እንዲለዩ አይፈቅድም፤ በሕይወታቸው በጣም ከባድ ነገር አጋጥሟቸው ሁሉ ነገር ጭልምልም እንዳለባቸው በሚሰማቸው ጊዜ እንኳ አብሯቸው ይሆናል።—ዕብራውያን 13:5, 6
-