-
‘ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ!’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
3. ይሖዋ “አገልጋዬ” ስላለው ሰው በኢሳይያስ አማካኝነት ምን ትንቢት ተናግሯል?
3 ይሖዋ እርሱ ራሱ የሚመርጠው አንድ አገልጋይ እንደሚመጣ በኢሳይያስ አማካኝነት ትንቢት ተናግሯል። “ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፣ በእርሱም ደስ የሚለኝ [“ነፍሴ የተቀበለችው፣” NW ] ምርጤ ይህ ነው፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል። አይጮኽም፣ ቃሉን ከፍ አያደርግም፤ ድምፁን በመንገድ ላይ በኀይል አያሰማም። የተቀጠቀጠ ሸምበቆ አይሰብርም፤ የሚጤስም የጧፍ ክር አያጠፋም፤ ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል። ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣ አይደክምም፤ ተስፋም አይቆርጥም፤ ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።”—ኢሳይያስ 42:1-4 አ.መ.ት
-
-
‘ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ!’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
6. ኢየሱስ እውነተኛው ፍትሕ ግልጽ ሆኖ እንዲታወቅ ያደረገው እንዴት ነው?
6 ኢየሱስ ግን አምላክ ስለ ፍትሕ ያለውን አመለካከት በግልጽ አስታውቋል። ያስተማረው ትምህርትም ሆነ አኗኗሩ እውነተኛው ፍትሕ በርኅራኄና በምሕረት ላይ የተመሠረተ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ነው። ዝነኛ የተራራ ስብከቱን ብቻ እንኳን ተመልከት። (ማቴዎስ ምዕራፍ 5-7) ፍትሕንና ጽድቅን እንዴት ማሳየት እንደሚገባ የሚጠቁም ድንቅ ማብራሪያ ነው! የወንጌል ዘገባዎችን ስናነብ ኢየሱስ ለድሆችና ለችግረኞች ያሳየው ርኅራኄ ልባችንን አይነካውምን? (ማቴዎስ 20:34፤ ማርቆስ 1:41፤ 6:34፤ ሉቃስ 7:13) እንደተቀጠቀጠ ሸንበቆ ጎብጠውና ደቅቀው ለነበሩት ሰዎች የሚያጽናና መልእክቱን አድርሶላቸዋል። እነዚህ ሰዎች የመኖር ተስፋቸው ሊጠፋ እንደተቃረበ የሚጤስ የጧፍ ክር ሆኖ ነበር። ኢየሱስ ‘የተቀጠቀጠን ሸንበቆ’ አልሰበረም፤ ‘የሚጤስንም የጧፍ ክር’ አላጠፋም። ይልቁንም ፍቅርና ርኅራኄ የተንጸባረቀበት ንግግሩና ድርጊቱ የዋህ የሆኑ ሰዎችን መንፈስ አነቃቅቶ ነበር።—ማቴዎስ 11:28-30
-