የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ደስ የሚሰኝበት አገልጋይ
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥር 15
    • 4 ኢየሱስ ገና ሕፃን እያለ ስምዖን የተባለ አንድ ጻድቅ ሰው በ⁠ኢሳይያስ 42:6 እና 49:6 ላይ አስቀድሞ በተነገረው መሠረት ‘ሕፃኑ ኢየሱስ’ “ሕዝቦችን የጋረደውን መሸፈኛ የሚገልጥ ብርሃን” እንደሚሆን በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ተናግሮ ነበር። (ሉቃስ 2:25-32) ከዚህም በላይ ኢየሱስ ለፍርድ በቀረበበት ምሽት ስለሚደርስበት ውርደት በ⁠ኢሳይያስ 50:6-9 ላይ አስቀድሞ ተነግሮ ነበር። (ማቴ. 26:67፤ ሉቃስ 22:63) በ33 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከተከበረው የጴንጤቆስጤ በዓል በኋላ ሐዋርያው ጴጥሮስ የይሖዋ ‘አገልጋይ’ ወይም ‘ባሪያ’ የተባለው ኢየሱስ መሆኑን በግልጽ ተናግሯል። (ኢሳ. 52:13፤ 53:11፤ የሐዋርያት ሥራ 3:13, 26⁠ን አንብብ። ) ስለ መሲሑ ከተነገሩት ከእነዚህ ትንቢቶች ምን እንማራለን?

  • ይሖዋ ደስ የሚሰኝበት አገልጋይ
    መጠበቂያ ግንብ—2009 | ጥር 15
    • “ብርሃን” እና “ቃል ኪዳን”

      11. በመጀመሪያው መቶ ዘመን ኢየሱስ ‘ለአሕዛብ ብርሃን’ የሆነው በምን መንገድ ነበር? ይህ ብርሃን እስከ ዘመናችን ድረስ የቀጠለውስ እንዴት ነው?

      11 በ⁠ኢሳይያስ 42:6 ላይ በሚገኘው ትንቢት መሠረት ኢየሱስ በእርግጥም ‘ለአሕዛብ ብርሃን’ ሆኗል። በምድራዊ አገልግሎቱ ወቅት በመጀመሪያ ለአይሁዳውያን መንፈሳዊ ብርሃን አብርቶላቸዋል። (ማቴ. 15:24፤ ሥራ 3:26) ሆኖም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” ብሎ ነበር። (ዮሐ. 8:12) በመሆኑም መንፈሳዊ ብርሃን በማብራት ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰው ዘር ፍጹም ሕይወቱን ቤዛ አድርጎ በመስጠት ጭምር ለአይሁድም ሆነ ለአሕዛብ ብርሃን ሆኗል። (ማቴ. 20:28) ኢየሱስ ትንሣኤ ካገኘ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን “እስከ ምድር ዳር ድረስ” ምሥክሮቹ እንዲሆኑ አዟቸዋል። (ሥራ 1:8) ጳውሎስና በርናባስ በአገልግሎታቸው ወቅት፣ “የአሕዛብ ብርሃን” የሚለውን አገላለጽ ከጠቀሱ በኋላ ይህ ሐሳብ አይሁዳዊ ባልሆኑ ሰዎች መካከል ያከናውኑት ከነበረው የስብከት ሥራ ጋር በተያያዘ ፍጻሜውን እንዳገኘ ገልጸዋል። (ሥራ 13:46-48፤ ከ⁠ኢሳይያስ 49:6 ጋር አወዳድር።) በምድር ላይ ያሉት የኢየሱስ ቅቡዓን ወንድሞችና አጋሮቻቸው፣ መንፈሳዊውን ብርሃን እያበሩ እንዲሁም ሰዎች “የአሕዛብ ብርሃን” በሆነው በኢየሱስ ላይ እምነት እንዲኖራቸው እየረዱ በመሆኑ ይህ ሥራ እስካሁን ድረስ ቀጥሏል።

      12. ይሖዋ፣ አገልጋዩን “ለሕዝቡ ቃል ኪዳን” ያደረገው እንዴት ነው?

      12 በዚሁ ትንቢት ላይ ይሖዋ፣ የመረጠውን አገልጋዩን “እጠብቅሃለሁ፤ ለሕዝቡ ቃል ኪዳን. . . አደርግሃለሁ” ብሎታል። (ኢሳ. 42:6) ሰይጣን፣ ኢየሱስን ለማጥፋትና በምድር ላይ የሚያከናውነውን አገልግሎት እንዳይፈጽም ለማገድ በተደጋጋሚ ጊዜያት ጥረት ቢያደርግም ይሖዋ፣ ኢየሱስ አልፎ እንዲሰጥ የወሰነው ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ጥበቃ አድርጎለታል። (ማቴ. 2:13፤ ዮሐ. 7:30) ከዚያም ይሖዋ፣ ኢየሱስን ከሞት በማስነሳት በምድር ላይ ለሚኖሩ ሰዎች “ቃል ኪዳን” አድርጎታል። ይህ የጸና ቃል ኪዳን፣ የአምላክ ታማኝ አገልጋይ በመንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ነፃ በማውጣት ‘ለአሕዛብ ብርሃን’ ሆኖ እንደሚቀጥል ያረጋግጣል።—ኢሳይያስ 49:8, 9⁠ን አንብብ።b

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ