- 
	                        
            
            ‘ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ!’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
- 
                            - 
                                        13. ይሖዋ ስለተመረጠ አገልጋዩ ምን ትንቢት ተናግሯል? 13 ኢሳይያስ እንዲህ በማለት ዘገባውን ይቀጥላል:- “ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፣ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፣ በእርስዋ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፣ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።” (ኢሳይያስ 42:5) ፈጣሪ የሆነውን ይሖዋን በተመለከተ የተሰጠ እንዴት ያለ ድንቅ መግለጫ ነው! ስለ ይሖዋ ኃይል የተሰጠው ይህ ማሳሰቢያ ከአፉ የሚወጣው ቃል ትልቅ ክብደት እንዲኖረው የሚያደርግ ነው። ይሖዋ እንዲህ ይላል:- “እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፣ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ፣ የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።”—ኢሳይያስ 42:6, 7 
 
- 
                                        
- 
	                        
            
            ‘ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ!’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
- 
                            - 
                                        15, 16. ኢየሱስ ‘ለአሕዛብ ብርሃን’ ሆኖ ያገለገለው በምን መንገድ ነው? 15 ተስፋ የተሰጠበት ይህ አገልጋይ ‘ለአሕዛብ ብርሃን’ እንደመሆኑ መጠን ‘የታወሩትን ዓይን ያበራል፣’ ‘በጨለማ የተቀመጡትንም’ ነፃ ያወጣል። ኢየሱስ ያደረገው ይህንኑ ነው። ስለ እውነት በመመሥከር የሰማያዊ አባቱን ስም አክብሯል። (ዮሐንስ 17:4, 6) የሐሰት ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን አጋልጧል፣ የመንግሥቱን ምሥራች ሰብኳል እንዲሁም በሃይማኖታዊ ግዞት የነበሩት ሰዎች መንፈሳዊ ነፃነት የሚያገኙበትን በር ከፍቷል። (ማቴዎስ 15:3-9፤ ሉቃስ 4:43፤ ዮሐንስ 18:37) የጨለማ ሥራን ከመሥራት እንዲርቁ ከማስጠንቀቁም ሌላ ሰይጣን ‘የሐሰት አባት’ እንዲሁም “የዚህ ዓለም ገዥ” መሆኑን አጋልጧል።—ዮሐንስ 3:19-21፤ 8:44፤ 16:11 16 ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” ሲል ተናግሯል። (ዮሐንስ 8:12) ፍጹም ሰብዓዊ ሕይወቱን ቤዛ አድርጎ ባቀረበ ጊዜ የዓለም ብርሃን መሆኑን ድንቅ በሆነ መንገድ አረጋግጧል። ይህን ቤዛ በመክፈሉም እምነት እንዳላቸው የሚያሳዩ ሰዎች የኃጢአት ይቅርታ ማግኘት፣ ከአምላክ ጋር ተቀባይነት ያለው ዝምድና መመሥረትና የዘላለም ሕይወት ተስፋን መጠባበቅ የሚችሉበትን በር ከፍቷል። (ማቴዎስ 20:28፤ ዮሐንስ 3:16) ኢየሱስ በሕይወት ዘመኑ በሙሉ ፍጹም ለአምላክ ያደረ መሆኑን በሚያሳይ መንገድ በመመላለስ የይሖዋን ሉዓላዊነት ሲያስከብር ዲያብሎስ ሐሰተኛ መሆኑን አረጋግጧል። በእርግጥም ኢየሱስ ለታወሩ ብርሃን የሚሰጥና በመንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ የታሠሩትን ነፃ የሚያወጣ ነው። 
 
-