የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላክ ማን ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 1. የአምላክ ስም ማን ነው? አምላክ ስሙን እንድናውቅ እንደሚፈልግስ በምን እናውቃለን?

      አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ራሱን ለእኛ አስተዋውቋል። “እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው” ብሏል። (ኢሳይያስ 42:5, 8⁠ን አንብብ።) “ይሖዋ” የሚለው ቃል ከዕብራይስጥ የተወሰደ ነው፤ ይህ ስም “እንዲሆን ያደርጋል” የሚል ትርጉም እንዳለው ይታመናል። ይሖዋ ስሙን እንድናውቅ ይፈልጋል። (ዘፀአት 3:15) ይህን በምን እናውቃለን? አምላክ ስሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከ7,000 ጊዜ በላይ እንዲጠቀስ አድርጓል!a ይሖዋ የሚለው ስም “በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር እውነተኛው አምላክ” ብቻ ሊጠራበት የሚችል ስም ነው።—ዘዳግም 4:39

  • አምላክ የሚቀበለው አምልኮ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 2. ይሖዋን ልናመልክ የሚገባው እንዴት ነው?

      ይሖዋ ፈጣሪያችን እንደመሆኑ መጠን ሊመለክ የሚገባው እሱ ብቻ ነው። (ራእይ 4:11) እሱን ብቻ መውደድ ይኖርብናል፤ እንዲሁም ምንም ዓይነት ቅርጻ ቅርጽ ወይም ምስል ሳንጠቀም ልናመልከው ይገባል።—ኢሳይያስ 42:8⁠ን አንብብ።

      አምልኳችን “ቅዱስና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው” መሆን ይኖርበታል። (ሮም 12:1) ይህም ሲባል እሱ ባወጣቸው የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መመራት አለብን ማለት ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ይሖዋን የሚወዱ ሰዎች እሱ ከጋብቻ ጋር በተያያዘ ያወጣውን መመሪያ ሊቀበሉና ሊታዘዙ ይገባል። በተጨማሪም ሲጋራ እንደማጨስ፣ ጫት እንደመቃም እንዲሁም ዕፆችን ወይም አልኮልን አላግባብ እንደመጠቀም ካሉ ጎጂ ልማዶች ይርቃሉ።a

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ