የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ”!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 11. ይሖዋ ለአገልጋዮቹ የሰጠው ተልዕኮ ምንድን ነው? ስለ አምላክነቱስ ምን ነገር ገልጧል?

      11 የሐሰት አማልክት ምንም ነገር የማድረግ ችሎታ ስለሌላቸው ምሥክሮች ማቅረብ አይችሉም። በመሆኑም ምሥክር ሆኖ የሚቀርብ አንድም ሰው በመጥፋቱ ያፍራሉ። አሁን ደግሞ ይሖዋ በተራው አምላክነቱን የሚያስመሰክርበት ጊዜ ደርሷል። ወደ ሕዝቡ በመመልከት እንዲህ ይላል:- “ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፣ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ . . .፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም። እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም። ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ አሳይቼማለሁ፣ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፤ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፣ . . . እኔም አምላክ ነኝ። ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፣ [እጄን] የሚከለክልስ ማን ነው?”​​—⁠⁠ኢሳይያስ 43:10-13

      12, 13. (ሀ) የይሖዋ ሕዝብ ምን ምሥክርነት መስጠት ይጠበቅበታል? (ለ) በዘመናችን የይሖዋ ስም የገነነው እንዴት ነው?

      12 ለዚህ የይሖዋ ቃል ምላሽ በመስጠት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ደስተኛ የሆኑ ምሥክሮች የምሥክርነት ቃል መስጫ ቦታውን ያጥለቀልቁታል። የሚሰጡት ምሥክርነት ግልጽና የማይታበል ነው። እንደ ኢያሱ ሁሉ እነርሱም ‘ይሖዋ የተናገረው በሙሉ እንደተፈጸመና ከቃሉ አንዳች እንዳልቀረ’ ይመሠክራሉ። (ኢያሱ 23:​14) በይሖዋ ሕዝብ ጆሮ የሚያቃጭለው ነገር ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤልና ሌሎችም ነቢያት እንደ አንድ ሰው ሆነው ስለ አይሁዳውያን ግዞትና በተአምራዊ መንገድ ነፃ ስለሚወጡበት ሁኔታ የተናገሩት ትንቢት ነው። (ኤርምያስ 25:​11, 12) አይሁዳውያንን ነፃ ያወጣው ቂሮስ በስም የተጠቀሰው ገና ከመወለዱ በፊት ነው!​—⁠ኢሳይያስ 44:​26 – 45:1

      13 ይህ ሁሉ ማስረጃ እያለ እውነተኛው አምላክ ይሖዋ ብቻ መሆኑን ማን ሊክድ ይችላል? ይሖዋ እንደ አረማዊ አማልክት ፍጡር አይደለም።a ከዚህ የተነሣ የይሖዋን ስም የተሸከሙት ሰዎች ስለ እርሱ ድንቅ ሥራዎች ወደፊት ለሚመጡት ትውልዶችም ሆነ ለሚጠይቋቸው ሁሉ የመንገር ልዩና አስደሳች መብት አግኝተዋል። (መዝሙር 78:​5-7) ዛሬ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮችም በተመሳሳይ በምድር ዙሪያ የይሖዋን ስም የማወጅ መብት አግኝተዋል። በ1920ዎቹ የነበሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ይሖዋ የሚለው የአምላክ ስም ያለውን ጥልቅ ትርጉም ተገነዘቡ። ከዚያም በሐምሌ 26, 1931 በኮሎምበስ፣ ኦሃዮ በተደረገ የአውራጃ ስብሰባ ላይ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት የነበረው ጆሴፍ ኤፍ ራዘርፎርድ “አዲስ ስም” የሚል ርዕስ ያለው የአቋም መግለጫ አቀረበ። “የይሖዋ ምሥክሮች በሚለው ስም መታወቅና በዚህ ስም መጠራት እንፈልጋለን” የሚሉት ቃላት የስብሰባውን ተካፋዮች በሙሉ ያስደሰቱ ሲሆን በሚያስተጋባ ድምፅ “አዎን!” በማለት የአቋም መግለጫውን መደገፋቸውን አሳይተዋል። ከዚያ ጊዜ አንስቶ የይሖዋ ስም በዓለም ዙሪያ በሰፊው ሊታወቅ ችሏል።​​—⁠⁠መዝሙር 83:​18 NW

  • “እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ”!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • a በብሔራት አፈ ታሪክ ውስጥ ብዙ አማልክት “እንደተወለዱ” እና “ልጆችንም” እንደወለዱ ይነገራል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ