-
“እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ”!የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
11. ይሖዋ ለአገልጋዮቹ የሰጠው ተልዕኮ ምንድን ነው? ስለ አምላክነቱስ ምን ነገር ገልጧል?
11 የሐሰት አማልክት ምንም ነገር የማድረግ ችሎታ ስለሌላቸው ምሥክሮች ማቅረብ አይችሉም። በመሆኑም ምሥክር ሆኖ የሚቀርብ አንድም ሰው በመጥፋቱ ያፍራሉ። አሁን ደግሞ ይሖዋ በተራው አምላክነቱን የሚያስመሰክርበት ጊዜ ደርሷል። ወደ ሕዝቡ በመመልከት እንዲህ ይላል:- “ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፣ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ . . .፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም። እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም። ተናግሬአለሁ አድኜማለሁ አሳይቼማለሁ፣ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፤ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፣ . . . እኔም አምላክ ነኝ። ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፣ [እጄን] የሚከለክልስ ማን ነው?”—ኢሳይያስ 43:10-13
-
-
“እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ”!የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
14. ይሖዋ፣ እስራኤላውያን የትኛውን ጉዳይ መለስ ብለው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል? ይህ ማሳሰቢያ ወቅታዊ የነበረውስ ለምንድን ነው?
14 ይሖዋ ስሙን በክብር የተሸከሙትን ሰዎች ‘እንደ ዓይኑ ብሌን’ ይንከባከባቸዋል። ከግብጽ እንዴት እንዳወጣቸውና በምድረ በዳ እንዴት ተንከባክቦ እንደመራቸው በመግለጽ እስራኤላውያን ይህን ጉዳይ መለስ ብለው እንዲያስቡ አድርጓቸዋል። (ዘዳግም 32:10, 12) በዚያ ወቅት የግብጻውያን አማልክት በሙሉ እንዴት እንደተዋረዱ በገዛ ዓይናቸው አይተው ስለነበር በመካከላቸው ባዕድ አማልክት አልነበሩም። አዎን፣ የግብጻውያን አማልክት ግብጽን መከላከልም ሆነ እስራኤላውያን እንዳይሄዱ ማገድ ሳይችሉ ቀርተዋል። (ዘጸአት 12:12) በተመሳሳይም ኃያሏ ባቢሎን በትንሹ እስከ 50 የሚደርሱ የሐሰት አማልክት ቤተ መቅደሶች ቢኖሯትም ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ሕዝቡን ነፃ በሚያወጣበት ጊዜ እጁን መከልከል አትችልም። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ከይሖዋ በቀር “የሚያድን የለም።”
-