-
ከዳተኛ ለሆነው የወይን ቦታ ወዮ!የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
29. ከእስራኤላውያን የተውጣጣውን የይሖዋ የወይን ቦታ ምን አስከፊ ፍጻሜ ይጠብቀዋል?
29 ኢሳይያስ ይህንን ትንቢታዊ መልእክት የሚደመድመው ‘የይሖዋን ሕግ የጣሉትና’ የጽድቅ ፍሬ ማፍራት የተሳናቸው ሰዎች መጨረሻቸው አስከፊ እንደሚሆን በመግለጽ ነው። (ኢሳይያስ 5:24፤ ሆሴዕ 9:16፤ ሚልክያስ 4:1) እንዲህ ይላል:- “[ይሖዋ] ለአሕዛብም [“ለአንድ ታላቅ ብሔር፣” NW] በሩቅ ምልክትን ያቆማል፣ ከምድርም ዳርቻ በፉጨት ይጠራቸዋል፤ እነሆም፣ እየተጣደፉ ፈጥነው ይመጣሉ።”—ኢሳይያስ 5:26፤ ዘዳግም 28:49፤ ኤርምያስ 5:15
30. በይሖዋ ሕዝቦች ላይ “አንድ ታላቅ ሕዝብ” የሚጠራው ማን ነው? ውጤቱስ ምን ይሆናል?
30 በጥንት ዘመን አንድ ረጅም እንጨት ከፍ ያለ ቦታ ላይ ይተከልና ሕዝቡ ወይም ሠራዊቱ ወደዚያ እንዲሰባሰብ ‘ምልክት’ ሆኖ ያገለግል ነበር። (ከኢሳይያስ 18:3፤ ኤርምያስ 51:27 ጋር አወዳድር።) አሁን ግን በስም ያልተጠቀሰውን ይህን “ታላቅ ብሔር” ፍርዱን ለማስፈጸም ሲል የሚሰበስበው ይሖዋ ራሱ ነው።b ‘በፉጨት ይጠራዋል’ ማለትም ሊቆጣጠራቸው እንደሚገባ በማሰብ ወደ ባዘኑት ሕዝቦቹ እንዲመጣ ትኩረቱን ይስበዋል ማለት ነው። ከዚያም ነቢዩ እንደ አንበሳ ያለው ይህ ድል አድራጊ በፍጥነት ስለሚያመጣው አስፈሪ ጥፋት ሲገልጽ ‘ንጥቂያውን’ ማለትም የአምላክን ብሔር ‘እንደሚይዝና’ በምርኮ ‘እንደሚወስደው’ ተናግሯል። (ኢሳይያስ 5:27-30ሀን አንብብ።) ይህ በይሖዋ ሕዝብ ምድር ለሚኖሩት ሰዎች እንዴት የሚያሳዝን ነገር ነው! “ወደ ምድርም ቢመለከቱ፣ እነሆ፣ ጨለማና መከራ አለ፤ ብርሃንም በደመናዎችዋ ውስጥ ጨልሞአል።”—ኢሳይያስ 5:30ለ
-
-
ከዳተኛ ለሆነው የወይን ቦታ ወዮ!የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
b ኢሳይያስ በሌሎች ትንቢቶች ውስጥ ባቢሎን የይሖዋን የጥፋት ፍርድ የሚያስፈጽም ብሔር እንደሆነ ገልጿል።
-