-
እውነተኛው አምላክ ሕዝቡን ነፃ እንደሚያወጣ ትንቢት ተናገረየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
20 “ከማኅፀን የሠራህ፣ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:- ሁሉን የፈጠርሁ፣ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ማን ነበረ? የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፣ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፣ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፤ የባሪያዬን ቃል አጸናለሁ፣ የመልእክተኞቼንም ምክር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌምን:- የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፣ የይሁዳንም ከተሞች:- ትታነጻላችሁ ፍራሾቻችሁንም አቆማለሁ እላለሁ፤ ቀላዩንም:- ደረቅ ሁን፣ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ እላለሁ፤ ቂሮስንም:- እርሱ እረኛዬ ነው፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን:- ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል እላለሁ።”—ኢሳይያስ 44:24-28
-
-
እውነተኛው አምላክ ሕዝቡን ነፃ እንደሚያወጣ ትንቢት ተናገረየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
22. የኤፍራጥስ ወንዝ የደረቀው እንዴት እንደሆነ አብራራ።
22 የአምላክ መንፈስ ድጋፍ የሌላቸው ምዋርተኞች ጊዜው ሲደርስ ልንጋለጥ እንችላለን ብለው ስለሚፈሩ ትንቢት በሚናገሩበት ጊዜ በዝርዝር ለመናገር አይደፍሩም። ይሖዋ ግን ሕዝቡ ወደ ትውልድ አገራቸው ተመልሰው ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሷን እንዲገነቡ ከምርኮ ነፃ ለማውጣት መሣሪያ አድርጎ የሚጠቀምበት ሰው ማን እንደሆነ ሳይቀር በኢሳይያስ አማካኝነት ለይቶ ጠቅሷል። ስሙ ቂሮስ ሲሆን የፋርሱ ታላቁ ቂሮስ በሚል ስያሜ ይታወቃል። ይሖዋ፣ ቂሮስ የባቢሎንን ግዙፍና ውስብስብ መከላከያ ጥሶ የሚገባበትን ስልት ሳይቀር በዝርዝር ተናግሯል። ባቢሎን በትላልቅ ቅጥሮች እንዲሁም በከተማዋ ውስጥና በዙሪያዋ በሚፈስሰው ውኃ የተከበበች ትሆናለች። ቂሮስ ለከተማዋ መከላከያ ቁልፍ ድርሻ ያለውን የኤፍራጥስ ወንዝ ለራሱ ዓላማ በሚበጅ መንገድ ይጠቀምበታል። የጥንቶቹ ታሪክ ጸሐፊዎች ሂሮዶተስ እና ዜኖፎን እንደዘገቡት ቂሮስ ከባቢሎን ትንሽ እልፍ ብሎ የኤፍራጥስን ወንዝ አቅጣጫ በማስቀየር የውኃው መጠን ወታደሮቹ በእግራቸው ሊሻገሩት እስኪችሉ ድረስ እንዲቀንስ አድርጓል። ባቢሎንን ከመከላከል አንጻር ሲታይ የኤፍራጥስ ወንዝ የደረቀ ያህል ነበር።
-