የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ትክክለኞቹን መልእክተኞች ለይቶ ማወቅ
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ግንቦት 1
    • 7, 8. ኢሳይያስ በመንፈስ ተነድቶ ስለ ባቢሎን ምን ተናግሯል? ይህስ ምን ማለት ነው?

      7 ይሁዳና ኢየሩሳሌም ለ70 ዓመታት ፍጹም ባድማና ኗሪ አልባ ሆነው መቆየት ነበረባቸው። ይሁን እንጂ ይሖዋ በኢሳይያስና በሕዝቅኤል አማካኝነት ከተማዋ እንደገና እንደምትሠራና ምድሪቱም አስቀድሞ በተነገረለት ትክክለኛ ጊዜ የሰዎች መኖሪያ እንደምትሆን ተናግሯል! ይህ በጣም አስገራሚ ትንቢት ነበር። ለምን? ባቢሎን እስረኞቿን ከእጅዋ እንደማታስወጣ ይነገርላት ስለነበር ነው። (ኢሳይያስ 14:​4, 15-17) ታዲያ እነዚህን ግዞተኞች ነፃ ሊያወጣቸው የሚችለው ማን ነው? ታላላቅ ቅጥሮች ያሏትንና በወንዝ የታጠረችውን ኃያልዋን ከተማ ባቢሎንን ማን ሊጥላት ይችላል? ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ ይችላል! ይህንኑ እንደሚያደርግ ተናግሯል:- “ቀላዩንም [ለከተማይቱ እንደ መከላከያ ሆኖ የሚያገለግለውን ውኃ ማለት ነው] ደረቅ ሁን፣ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ እላለሁ፤ ቂሮስንም:- እርሱ እረኛዬ ነው፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን:- ትታነጺያለሽ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል እላለሁ።”​— ኢሳይያስ 44:​25, 27, 28

      8 እስቲ ገምቱት! ኤፍራጥስ የሰው ኃይል በቀላሉ የሚደፍረው ወንዝ አልነበረም። በይሖዋ ፊት ግን በፍም ላይ ጠብ እንዳለ የውኃ ጠብታ ትሽ! ብሎ ወዲያው እንደሚጠፋ ያህል ነው። ባቢሎን ትወድቃለች። ፋርሳዊው ቂሮስ ከመወለዱ ከ150 ዓመት በፊት ይሖዋ በኢሳይያስ አማካኝነት ይህ ንጉሥ ባቢሎንን ድል አድርጎ በመያዝ አይሁዳውያን ግዞተኞችን ነፃ እንደሚያወጣና ወደ አገራቸው ተመልሰው ኢየሩሳሌምንና ቤተ መቅደሷን እንዲገነቡ ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ተንብዮ ነበር።

  • ትክክለኞቹን መልእክተኞች ለይቶ ማወቅ
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ግንቦት 1
    • 11. የባቢሎን ነዋሪዎች ተማምነውና ተረጋግተው የተቀመጡት ለምን ነበር?

      11 ቂሮስ በባቢሎን ላይ በዘመተ ጊዜ የባቢሎን ነዋሪዎች ተማምነውና አለምንም ሥጋት ተቀምጠው ነበር። ከተማቸው ዙሪያዋን በኤፍራጥስ ወንዝ አማካኝነት በተሠራ ስፋትና ጥልቀት ባለው በውኃ የተሞላ ጉድጓድ የተከበበች ነበረች። ከተማይቱን መሐል ለመሐል አቋርጦ ከሚያልፈው ወንዝ በስተ ምሥራቅ የተገነባ መተላለፊያ ነበረ። ናቡከደነፆር ይህን መተላለፊያ ከከተማይቱ ለመለየት ሲል ራሱ እንደተናገረው “ልክ እንደ ተራራ ሊነቃነቅ [የማይችል] . . . ተራራ የሚያህል ከፍታ ያለው ቅጥር” ሠርቶ ነበር።a ይህ ቅጥር ግዙፍ የሆኑ የነሐስ በሮች ነበሩት። በበሮቹ ለመግባት የፈለገ ሰው ከወንዙ ዳርቻ ላይ ያለውን መወጣጫ መውጣት ይኖርበታል። በባቢሎን ግዞተኛ ሆነው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ነጻ ልንወጣ እንችላለን የሚል ተስፋ ሊኖራቸው አለመቻሉ ምንም አያስደንቅም!

      12, 13. ባቢሎን በቂሮስ እጅ በወደቀች ጊዜ ይሖዋ በመልእክተኛው በኢሳይያስ በኩል የተናገረው ቃል የተፈጸመው እንዴት ነው?

      12 ይሁን እንጂ በይሖዋ ላይ እምነት የነበራቸው አይሁዳውያን ግዞተኞች ተስፋ አልቆረጡም! ብሩሕ ተስፋ ነበራቸው። አምላክ በነቢያቱ አማካኝነት ነፃ እንደሚያወጣቸው ቃል ገብቶ ነበር። ታዲያ አምላክ የገባውን ቃል የፈጸመው እንዴት ነው? ቂሮስ ወታደሮቹ ከባቢሎን በስተ ሰሜን ብዙ ኪሎ ሜትሮች ራቅ ብለው የኤፍራጥስ ወንዝ አቅጣጫውን ለውጦ እንዲፈስ እንዲያደርጉ አዘዘ። ዋነኛው የከተማይቱ መከላከያ በአንፃራዊ ሁኔታ ውኃው ተሟጥጦ ያለቀበት ጐድጓዳ ሥፍራ ሆነ። በዚያ ወሳኝ የሆነ ምሽት በመጠጥ ሲራጩ የነበሩት ባቢሎናውያን በግዴለሽነት በኤፍራጥስ ወንዝ ዳርቻ የነበሩትን ባለ ሁለት ተካፋች በሮች ሳይዘጉ ቀሩ። ይሖዋ ቃል በቃል የነሐስ በሮቹ እንዲሰባበሩ ወይም የበሮቹ መወርወሪያ እንዲቆራረጥ አላደረገም፤ ይሁን እንጂ በሚያስገርም ሁኔታ በሮቹ ክፍት ሆነው እንዲያድሩ ማድረጉ ተመሳሳይ የሆነ ውጤት ነበረው። የባቢሎን ቅጥሮች ምንም የፈየዱት ነገር አልነበረም! የቂሮስ ጭፍሮች ለቅጥሩ መወጣጫ መሥራት ሳያስፈልጋቸው ዘልቀው ገቡ። ይሖዋ ከቂሮስ ፊት እየሄደ ‘ተራራውን’ ማለትም እንቅፋቱን ሁሉ አስወገደለት። ኢሳይያስ የአምላክ እውነተኛ መልእክተኛ መሆኑ ተረጋገጠ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ