-
በሐሰት ሃይማኖት ላይ ድንገተኛ ጥፋት እንደሚደርስ ተተነበየየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
12. ባቢሎን “ቅምጥል” ተብላ የተጠራችው ለምንድን ነው?
12 ይሖዋ እንዲህ ሲል አስታወቀ:- “አሁንም አንቺ ቅምጥል ተዘልለሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም:- እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም የወላድ መካንነትንም አላውቅም የምትዪ ይህን ስሚ።” (ኢሳይያስ 47:8) ባቢሎናውያን ለሥጋዊ ምኞቶቻቸው ያደሩ ቅምጥሎች ነበሩ። በአምስተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ ይኖር የነበረው ታሪክ ጸሐፊው ሂሮዶተስ ባቢሎናውያን “እጅግ አሳፋሪ የሆነ ልማድ” እንደነበራቸው ገልጿል። ሁሉም ሴቶች ለፍቅር የሴት አምላካቸው ያላቸውን አክብሮት ለማሳየት ዝሙት መፈጸም ይጠበቅባቸው ነበር። በተመሳሳይም ጥንታዊው ታሪክ ጸሐፊ ኩርቲየስ እንዲህ ብሏል:- “የከተማይቱ የሥነ ምግባር ደረጃ በእጅጉ ያዘቀጠ ነበር። በዚያ የነበረውን ያህል ወራዳ ለሆነ የብልግና ድርጊት የሚጋብዝና የሚያነሳሳ ብልሹ ሥርዓት የለም።”
13. ባቢሎን ለሥጋዊ ነገሮች ያደረች መሆኗ ውድቀቷን የሚያፋጥነው እንዴት ነው?
13 ባቢሎን ለሥጋዊ ነገሮች ያደረች መሆኗ ውድቀቷን ይበልጥ ያፋጥነዋል። በውድቀቷ ዋዜማ ንጉሷና መኳንንቱ በታላቅ ድግስ በመታደም አቅላቸውን እስኪስቱ ይጠጣሉ። በመሆኑም የሜዶ ፋርስ ሠራዊት ከተማይቱን ሲወርር አንዳች የሚያውቁት ነገር አይኖርም። (ዳንኤል 5:1-4) ባቢሎን የማይደፈሩ የሚመስሉት ግንቦቿና በከተማይቱ ዙሪያ ያለው ውኃ ከወራሪ ኃይል እንደሚጠብቋት በመተማመን ‘ተዘልላ ትቀመጣለች።’ በልቧም ሥልጣኗን ሊወስድ የሚችል ‘እንደሌለ’ አድርጋ ታስባለች። ንጉሠ ነገሥቷንም ሆነ ‘ልጆችዋን’ ወይም ሕዝቧን በማጣት “መበለት” ልትሆን እንደምትችል አይታያትም። ይሁን እንጂ ከይሖዋ አምላክ የበቀል እርምጃ ሊያድናት የሚችል ግንብ ሊኖር አይችልም! ይሖዋ ቆየት ብሎ “ባቢሎን ምንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፣ የኃይልዋንም ከፍታ ብታጸና፣ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል” ሲል ተናግሯል።—ኤርምያስ 51:53
-
-
በሐሰት ሃይማኖት ላይ ድንገተኛ ጥፋት እንደሚደርስ ተተነበየየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
[በገጽ 111 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]
ቅምጥሏ ባቢሎን ትቢያ ላይ ትጣላለች
-