የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በሐሰት ሃይማኖት ላይ ድንገተኛ ጥፋት እንደሚደርስ ተተነበየ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 14. ባቢሎን ‘የወላድ መካንና መበለት’ የምትሆነው በምን መንገዶች ነው?

      14 ባቢሎን ምን ይደርስባታል? ይሖዋ በመቀጠል እንዲህ ሲል ይገልጻል:- “አሁን ግን በአንድ ቀን እነዚህ ሁለት ነገሮች፣ የወላድ መካንነትና መበለትነት፣ በድንገት ይመጡብሻል፤ ስለ መተቶችሽ ብዛትና ስለ አስማቶችሽ ጽናት ፈጽመው ይመጡብሻል።” (ኢሳይያስ 47:9) አዎን፣ ባቢሎን በዓለም ላይ የተቆናጠጠችውን ታላቅ ሥልጣን በድንገት ታጣለች። በጥንቶቹ ምሥራቃውያን አገሮች መበለትና የወላድ መካን የሆነች ሴት ከሁሉ የከፋ መቅሰፍት እንደደረሰባት ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ባቢሎን በወደቀችበት ሌሊት ምን ያህል ‘ልጆች’ እንዳጣች የምናውቀው ነገር የለም።d ይሁን እንጂ ውሎ አድሮ ከተማዋ ከናካቴው ሰው አልባ እንደምትሆን ተተንብዮ ነበር። (ኤርምያስ 51:​29) በተጨማሪም ነገሥታቷ ከዙፋን የሚወርዱ በመሆኑ መበለት ትሆናለች።

      15. ባቢሎን በአይሁዳውያን ላይ ከፈጸመችው ግፍ በተጨማሪ ይሖዋን ያስቆጣው ነገር ምንድን ነው?

      15 ይሁን እንጂ ይሖዋ በባቢሎን ላይ የተቆጣው በአይሁዳውያን ላይ በፈጸመችው ግፍ ብቻ አይደለም። ‘የመተትዋ ብዛትም’ አስቆጥቶታል። አምላክ ለእስራኤላውያን የሰጠው ሕግ መናፍስታዊ እምነቶችን የሚያወግዝ ቢሆንም ባቢሎን በአስማት ድርጊቶች የተሞላች ነበረች። (ዘዳግም 18:​10–12፤ ሕዝቅኤል 21:​21) ሶሻል ላይፍ አማንግ ዚ አሲሪያንስ ኤንድ ባቢሎኒያንስ የተባለው መጽሐፍ ባቢሎናውያን “ሥፍር ቁጥር በሌላቸው አጋንንት እንደተከበቡ አድርገው በማሰብ በከፍተኛ ፍርሃት ተውጠው ይኖሩ” እንደነበረ ይገልጻል።

  • በሐሰት ሃይማኖት ላይ ድንገተኛ ጥፋት እንደሚደርስ ተተነበየ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • d  በሬይመንድ ፊሊፕ ዶውረቲ የተዘጋጀው ናቦኒደስ ኤንድ ቤልሻዘር የተሰኘው መጽሐፍ እንደገለጸው የናቦኒደስ ዜና መዋዕል ባቢሎንን የወረረው ሠራዊት “ያላንዳች ውጊያ” ወደከተማይቱ እንደዘለቀ ቢናገርም ግሪካዊው ታሪክ ጸሐፊ ዜኖፎን ግን ከፍተኛ የሆነ እልቂት ደርሶ ሊሆን እንደሚችል አመልክቷል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ