የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ታኅሣሥ 1
    • የይሖዋ አምላክን ማንነት በአንድ ቃል መግለጽ ቢያስፈልግህ የትኛውን ቃል ትመርጣለህ? በስምንተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. ነቢዩ ኢሳይያስ፣ የተወሰኑ መንፈሳዊ ፍጥረታት የይሖዋን ማንነት ጥሩ አድርጎ የሚገልጽ ቃል ተጠቅመው ሲያወድሱት በራእይ ተመልክቶ ነበር፤ የተጠቀሙበት ቃል “ቅዱስ” የሚል ነው። ኢሳይያስ ያየውና የሰማው ነገር የአድናቆት ስሜት እንዲሰማንና ወደ ይሖዋ ይበልጥ እንድንቀርብ ሊያነሳሳን ይገባል። በ⁠ኢሳይያስ 6:1-3 ላይ ያለውን ሐሳብ ስንመረምር አንተም በቦታው ላይ እንዳለህ አድርገህ አስብ።

  • “ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው”
    መጠበቂያ ግንብ—2011 | ታኅሣሥ 1
    • ከዚያም ኢሳይያስ ምናልባትም ማንም ሰው በራእይ አይቶት የማያውቀውን ነገር ተመለከተ። እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “ሱራፌልም ከእርሱ [ከይሖዋ] በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፍ ነበራቸው። በሁለት ክንፍ ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለት ክንፍ እግራቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፍ ይበሩ ነበር።” (ቁጥር 2) ሱራፌል ከፍተኛ ቦታ ያላቸው መንፈሳዊ ፍጡራን ናቸው። እነዚህን መንፈሳዊ ፍጡራን የጠቀሰው ብቸኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ኢሳይያስ ነው። ሱራፌል ይሖዋ የሚያዘውን ማንኛውንም ነገር ለመፈጸም ምንጊዜም ዝግጁዎች ናቸው። ፊታቸውንና እግራቸውን መሸፈናቸው አምላክን እንደሚያመልኩና እንደሚያከብሩ የሚያሳይ ከመሆኑም ሌላ በፊቱ ሆነው እሱን የማገልገል መብታቸውን ከፍ አድርገው እንደሚመለከቱት የሚጠቁም ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ