-
“ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው”መጠበቂያ ግንብ—2011 | ታኅሣሥ 1
-
-
የይሖዋ አምላክን ማንነት በአንድ ቃል መግለጽ ቢያስፈልግህ የትኛውን ቃል ትመርጣለህ? በስምንተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. ነቢዩ ኢሳይያስ፣ የተወሰኑ መንፈሳዊ ፍጥረታት የይሖዋን ማንነት ጥሩ አድርጎ የሚገልጽ ቃል ተጠቅመው ሲያወድሱት በራእይ ተመልክቶ ነበር፤ የተጠቀሙበት ቃል “ቅዱስ” የሚል ነው። ኢሳይያስ ያየውና የሰማው ነገር የአድናቆት ስሜት እንዲሰማንና ወደ ይሖዋ ይበልጥ እንድንቀርብ ሊያነሳሳን ይገባል። በኢሳይያስ 6:1-3 ላይ ያለውን ሐሳብ ስንመረምር አንተም በቦታው ላይ እንዳለህ አድርገህ አስብ።
-
-
“ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው”መጠበቂያ ግንብ—2011 | ታኅሣሥ 1
-
-
ኢሳይያስ በአድናቆት ስሜት እንዲዋጥ ያደረገው ያየው ነገር ብቻ ሳይሆን የሰማውም ነገር ነው። ሱራፌል በሰማይ እንዳለ የመዘምራን ቡድን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይዘምሩ ነበር። ኢሳይያስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “አንዳቸውም ለሌላው ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው። . . .’ ይሉ ነበር።” (ቁጥር 3 NW) “ቅዱስ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ንጹሕና የጠራ የሚል ሐሳብ ያስተላልፋል። በተጨማሪም ቃሉ “ከኃጢአት ድርጊት ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆንን እንዲሁም መለየትን” ያመለክታል። ሱራፌል እርስ በርስ በመቀባበል በመዝሙራቸው ላይ “ቅዱስ” የሚለውን ቃል ሦስት ጊዜ መጥቀሳቸው ይሖዋ በቅድስናው አቻ የማይገኝለት ለመሆኑ አጽንኦት ለመስጠት አስችሏል። (ራእይ 4:8) እንግዲያው ቅድስና የይሖዋ ማንነት ዋነኛ መገለጫ ነው ሊባል ይችላል። ይሖዋ ሙሉ በሙሉ የጠራ፣ ንጹሕና እንከን የማይገኝበት ነው።
-