የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ የሚያስተምረን ለጥቅማችን ነው
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 19. ይሖዋ ምን ፍቅራዊ ግብዣ አቅርቧል?

      19 ይሖዋ ቀጥሎ የተናገራቸው ልብ የሚነኩ ቃላት ሕዝቡ ከመከራ እንዲጠበቁና በደስታ እንዲኖሩ የሚፈልግ መሆኑን የሚያመለክቱ ናቸው:- “ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር።” (ኢሳይያስ 48:18) ሁሉን ቻይ ከሆነው ፈጣሪ የቀረበ እንዴት ያለ ፍቅራዊ ግብዣ ነው! (ዘዳግም 5:​29፤ መዝሙር 81:​13) እስራኤላውያን ትእዛዙን ቢሰሙ ወደ ግዞት በመሄድ ፋንታ እንደ ወንዝ ውኃ የተትረፈረፈ ሰላም ሊያገኙ ይችላሉ። (መዝሙር 119:​165) የጽድቅ ሥራዎቻቸውም እንደ ባሕር ሞገድ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ይሆናሉ። (አሞጽ 5:​24) ይሖዋ ለእነሱ ካለው አሳቢነት የተነሳ ሊሄዱበት የሚገባውን መንገድ በማሳየት እንዲሰሙት ተማጽኗቸዋል። ቢሰሙት ምንኛ ይጠቀሙ ነበር!

  • ይሖዋ የሚያስተምረን ለጥቅማችን ነው
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 21. በዘመናችን የይሖዋን መመሪያ ለማግኘት መጣራችን ምን በረከቶች ሊያስገኝልን ይችላል?

      21 ዛሬ ያሉት የይሖዋ አምላኪዎችም ኃይለኛ መልእክት ባዘለው በዚህ ምንባብ ውስጥ የሰፈሩትን መሠረታዊ ሥርዓቶች ማክበር ይኖርባቸዋል። ይሖዋ የሕይወት ምንጭ በመሆኑ ሕይወታችንን እንዴት ልንጠቀምበት እንደሚገባ ከማንም በላይ የሚያውቀው እርሱ ነው። (መዝሙር 36:​9) ያወጣቸው መመሪያዎች ደስታችንን የሚሰርቁ ሳይሆኑ ለእኛው ሕይወት የሚበጁ ናቸው። እውነተኛ ክርስቲያኖች ከይሖዋ ለመማር ጥረት በማድረግ ለዚህ ያላቸውን አድናቆት ያሳያሉ። (ሚክያስ 4:​2) ይሖዋ የሚሰጠን መመሪያ መንፈሳዊነታችን እና ከእርሱ ጋር ያለን ዝምድና እንዲጠበቅ የሚያደርግ ከመሆኑም ሌላ አቋማችንን ሊያበላሽ የሚችለውን የሰይጣን ተጽዕኖ መቋቋም እንድንችል ይረዳናል። የአምላክ ሕግጋት የተመሠረቱባቸውን መሠረታዊ ሥርዓቶች ጠለቅ ብለን ስናስተውል ይሖዋ የሚያስተምረን ለእኛው ጥቅም እንደሆነ እንገነዘባለን። ‘ትእዛዛቱም ከባዶች እንዳልሆኑ’ እንረዳለን። ይህም ከጥፋት እንድንጠበቅ ይረዳናል።​—⁠1 ዮሐንስ 2:​17፤ 5:​3

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ