የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘አምላክ በጎ ፈቃድ ያሳየበት ዘመን’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 8. የገዛ አገሩ ሰዎች ለመሲሑ የሚኖራቸው አመለካከት ምን ይመስላል? ሆኖም መሲሑ ስኬታማነቱ የሚመዘነው በማን ነው?

      8 ይሁን እንጂ ከገዛ አገሩ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ኢየሱስን በመናቅ ፊታቸውን አዙረውበት የለምን? አዎን፣ በጥቅሉ ሲታይ የእስራኤል ሕዝብ ኢየሱስን በአምላክ የተቀባ አገልጋይ አድርገው አይቀበሉትም። (ዮሐንስ 1:​11) ኢየሱስ በምድር ላይ የሚያከናውናቸው ነገሮች በሙሉ በዘመኑ በነበሩት ሰዎች ዓይን ከንቱና ምንም ዋጋ እንደሌላቸው ተደርገው ይታያሉ። መሲሑ ቀጥሎ የተናገራቸው ቃላት አገልግሎቱ እንዲህ ያለ ሁኔታ እንደሚገጥመው የሚጠቁሙ ናቸው:- “በከንቱ ደከምሁ፣ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጉልበቴን ፈጀሁ።” (ኢሳይያስ 49:4ሀ) መሲሑ እነዚህን ቃላት የተናገረው የተስፋ መቁረጥ ስሜት አድሮበት አይደለም። ቀጥሎ ምን እንዳለ ልብ በል:- “ፍርዴ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ፣ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው።” (ኢሳይያስ 49:4ለ) የመሲሑ ስኬታማነት የሚመዘነው በሰዎች ሳይሆን በአምላክ ነው።

  • ‘አምላክ በጎ ፈቃድ ያሳየበት ዘመን’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 10 በዘመናችን ያሉት የኢየሱስ ተከታዮች አንዳንድ ጊዜ በከንቱ እየደከሙ እንዳሉ ሆኖ ሊሰማቸው ይችላል። በአንዳንድ ቦታዎች በአገልግሎት የሚያገኙት ውጤት ከሥራቸውና ከድካማቸው ጋር ሲነጻጸር ከቁጥር የማይገባ ሆኖ ሊታይ ይችላል። ይሁንና ኢየሱስ የተወውን ምሳሌ በመኮረጅ በአገልግሎታቸው ይጸናሉ። በተጨማሪም ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፋቸው የሚከተሉት ቃላት ጥሩ ማበረታቻ ይሆኑላቸዋል:- “ስለዚህ፣ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፣ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፣ የማትነቃነቁም፣ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ።”​—⁠1 ቆሮንቶስ 15:58

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ