የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘አምላክ በጎ ፈቃድ ያሳየበት ዘመን’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 22. ይሖዋ ሕዝቡን እንደማይረሳ ጠበቅ አድርጎ የገለጸው እንዴት ነው?

      22 ኢሳይያስ አሁን የይሖዋን ቃል ማሰማቱን ይቀጥላል። በግዞት የሚኖሩት እስራኤላውያን የመታከትና ተስፋ የመቁረጥ ዝንባሌ እንደሚታይባቸው በመግለጽ እንዲህ ሲል ተነበየ:- “ጽዮን ግን:- እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች።” (ኢሳይያስ 49:14) ይህ እውነት ነውን? ይሖዋ ሕዝቡን እርግፍ አድርጎ በመተው ከናካቴው ረስቷቸዋልን? ኢሳይያስ የይሖዋ ቃል አቀባይ በመሆን እንዲህ ሲል መናገሩን ቀጠለ:- “በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፣ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም።” (ኢሳይያስ 49:15) ይሖዋ ለሕዝቡ ያለውን ፍቅር የሚያሳይ እንዴት ያለ ግሩም ምላሽ ነው! አምላክ ለሕዝቡ ያለው ፍቅር እናት ለልጅዋ ካላት ፍቅር የላቀ ነው። ታማኝ የሆኑትን አገልጋዮቹን ዘወትር ያስባል። ስማቸው በእጁ ላይ የተቀረጸ ያህል ያስታውሳቸዋል:- “እነሆ፣ እኔ በእጄ መጻፍ ቀርጬሻለሁ፣ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።”​—⁠ኢሳይያስ 49:16

      23. ጳውሎስ፣ ይሖዋ ፈጽሞ እንደማይረሳቸው ሙሉ እምነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ክርስቲያኖችን ያሳሰበው እንዴት ነው?

      23 ሐዋርያው ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ “ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት” ሲል ክርስቲያኖችን አጥብቆ አሳስቧቸዋል። (ገላትያ 6:9) ለዕብራውያን ክርስቲያኖች ደግሞ የሚከተሉትን አበረታች ቃላት ጽፎላቸዋል:- “እግዚአብሔር . . . ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።” (ዕብራውያን 6:10) ይሖዋ ሕዝቡን እንደረሳ ሆኖ ፈጽሞ ሊሰማን አይገባም። ልክ እንደ ጥንቷ ጽዮን ዛሬ ያሉ ክርስቲያኖችም የሚደሰቱበትና ይሖዋን በትዕግሥት የሚጠባበቁበት በቂ ምክንያት አላቸው። ይሖዋ ቃል ኪዳኑንም ሆነ የሰጠውን ተስፋ መፈጸሙ አይቀርም።

  • ‘አምላክ በጎ ፈቃድ ያሳየበት ዘመን’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 25. በዘመናችን መንፈሳዊ እስራኤል ቀድሞ ወደነበረችበት ሁኔታ የተመለሰችው እንዴት ነው?

      25 እነዚህ ቃላት በዘመናችንም ተፈጽመዋል። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በነበሩት አስቸጋሪ ዓመታት መንፈሳዊ እስራኤል ተማርካና ውድማ ሆና ነበር። ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ ቀድሞ ወደነበረችበት ሁኔታ በመመለስ መንፈሳዊ ገነት ሆናለች። (ኢሳይያስ 35:​1-10) ኢሳይያስ እንደጠቀሳት በአንድ ወቅት ባድማ ሆና እንደነበረችው ከተማ ደስተኛና ትጉ በሆኑ የይሖዋ አምላኪዎች በመጥለቅለቋ ሐሴት አድርጋለች።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ