-
‘አምላክ በጎ ፈቃድ ያሳየበት ዘመን’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
28. (ሀ) ይሖዋ ሕዝቡ ነፃ እንደሚወጡ በድጋሚ ያረጋገጠው ምን በማለት ነው? (ለ) ዛሬም ቢሆን ይሖዋ ሕዝቡን በተመለከተ የትኛውን ቃሉን ይጠብቃል?
28 በባቢሎን በግዞት ከሚኖሩት መካከል አንዳንዶቹ ‘እውን እስራኤል ነፃ ልትወጣ ትችላለች?’ ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ። ይሖዋ ይህን ጥያቄ ግምት ውስጥ በማስገባት እንዲህ ሲል ይጠይቃል:- “በውኑ ብዝበዛ ከኃያል እጅ ይወሰዳልን? ወይስ የጨካኙ ምርኮኞች ያመልጣሉን?” (ኢሳይያስ 49:24) መልሱ አዎን፣ የሚል ነው። ይሖዋ እንዲህ ሲል ያረጋግጥላቸዋል:- “በኃያላን የተማረኩ ይወሰዳሉ፣ የጨካኞችም ብዝበዛ ያመልጣል።” (ኢሳይያስ 49:25ሀ) ይህ እንዴት ያለ የሚያጽናና ዋስትና ነው! ከዚህም በተጨማሪ ይሖዋ ለሕዝቡ በጎ ፈቃድ ለማሳየት ብቻ ሳይሆን ጥበቃም ለማድረግ ቃል ገብቷል። በማያሻማ ቃል እንዲህ ሲል ተናገረ:- “ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፣ ልጆችሽንም አድናለሁ።” (ኢሳይያስ 49:25ለ) ይህ ቃል ዛሬም እንደተጠበቀ ነው። በዘካርያስ 2:8 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው ይሖዋ ‘የሚነካችሁ የዓይኔን ብሌን የሚነካ ነውና’ ሲል ተናግሯል። እርግጥ ነው፣ ዛሬ አምላክ በጎ ፈቃዱን እያሳየ ባለበት ዘመን ላይ የምንገኝ በመሆኑ በምድር ዙሪያ ያሉ ሰዎች ወደ መንፈሳዊቷ ጽዮን መጉረፍ የሚችሉበት አጋጣሚ አላቸው። ይሁን እንጂ ይህ የበጎ ፈቃድ ዘመን የሚያከትምበት ጊዜ ይመጣል።
-
-
‘አምላክ በጎ ፈቃድ ያሳየበት ዘመን’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
30. ይሖዋ ሕዝቡን ለማዳን ምን እርምጃዎችን ወስዷል? ወደፊትስ ምን እርምጃ ይወስዳል?
30 እነዚህ ቃላት የመጀመሪያ ፍጻሜያቸውን ያገኙት ይሖዋ ቂሮስን በመጠቀም ሕዝቡን ከባቢሎን ግዞት ነፃ ባወጣቸው ጊዜ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በ1919 ይሖዋ በዙፋን ላይ የተቀመጠውን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን በመጠቀም ሕዝቡን ከመንፈሳዊ ባርነት ባላቀቀበት ጊዜ በተመሳሳይ ሁኔታ ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋም ሆነ ኢየሱስ አዳኝ እንደሆኑ ይናገራል። (ቲቶ 2:11-13፤ 3:4-6) ይሖዋ አዳኛችን ሲሆን መሲሑ ኢየሱስ ደግሞ ‘ዋነኛ ወኪሉ [NW ]’ ነው። (ሥራ 5:31) በእርግጥም አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የወሰዳቸው የማዳን እርምጃዎች እጅግ አስደናቂ ናቸው። ይሖዋ በምሥራቹ አማካኝነት ቅን ልብ ያላቸውን ሰዎች ከሐሰት ሃይማኖት ባርነት ነፃ ያወጣል። በቤዛው መሥዋዕት አማካኝነት ደግሞ ከኃጢአትና ከሞት ባርነት ያላቅቃቸዋል። በ1919 የኢየሱስን ወንድሞች ከመንፈሳዊ ባርነት ነፃ አውጥቷቸዋል። በጣም እየቀረበ ባለው የአርማጌዶን ጦርነት ደግሞ እጅግ ብዙ የሆኑ ታማኝ ሰዎችን በኃጢአተኞች ላይ ከሚደርሰው ጥፋት ያድናቸዋል።
-