-
“በአለቆች አትታመኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
5 በግብጽ መታመን የመረጡት ከይሖዋ የበለጠ አስተማማኝ የሆነ የማዳን ኃይል ኖሯት ነውን? እነዚህ ከዳተኛ አይሁዳውያን ከብዙ መቶ ዘመናት በፊት የእስራኤል ሕዝብ ራሱን የቻለ ብሔር ሆኖ እንዲቋቋም ያስቻሉትን ሁኔታዎች የዘነጉ ይመስላል። ይሖዋ የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበላቸው:- “መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝምን? እነሆ፣ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፣ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዓሦቻቸው ይገማሉ በጥማትም ይሞታሉ። ሰማያትን ጥቁረት አለብሳቸዋለሁ፣ መጋረጃቸውንም ማቅ አደርጋለሁ።”—ኢሳይያስ 50:2ለ, 3
-
-
“በአለቆች አትታመኑ”የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
7 ይሖዋ በግብጻውያንና በእስራኤላውያን መካከል የደመና ዓምድ በማቆም ግብጻውያን ወደፊት እንዳይገሰግሱ አገዳቸው። ግብጻውያን በጨለማ ሲዋጡ እስራኤላውያን ግን በብርሃን ይጓዙ ነበር። (ዘጸአት 14:20) በዚህ መንገድ ይሖዋ ግብጻውያንን ባሉበት እንዲቆሙ ካደረገ በኋላ “ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምሥራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፣ ባሕሩንም አደረቀው።” (ዘጸአት 14:21) ውኃው ለሁለት ሲከፈል ሕዝቡ ሁሉ ይኸውም ወንዶቹ፣ ሴቶቹና ሕፃናቱ በሙሉ ቀይ ባሕርን ያላንዳች ችግር ተሻገሩ። ይሖዋ ሕዝቡ ባሕሩን ተሻግረው ሊጨርሱ ጥቂት ሲቀራቸው ደመናውን አነሳው። ግብጻውያን እስራኤላውያንን አሳድደው ለመያዝ እየተንደረደሩ ወደተከፈለው ባሕር ገቡ። ይሖዋ ሕዝቡ ሙሉ በሙሉ ከተሻገሩ በኋላ ውኃው እንደገና እንዲፈስ በማድረግ ፈርዖንና ሠራዊቱን አሰጠማቸው። በዚህ መንገድ ይሖዋ ለሕዝቡ ተዋጋ። ይህ ዛሬ ላሉ ክርስቲያኖች እንዴት ያለ ግሩም ማበረታቻ ነው!—ዘጸአት 14:23-28
-