የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በአለቆች አትታመኑ”
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 13. ኢየሱስ ከፊቱ ምን ይጠብቀዋል? ሆኖም ደፋር መሆኑን የሚያሳየው እንዴት ነው?

      13 የይሖዋን አንድያ ልጅ ለመቀበል አሻፈረን ከሚሉት ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ ኢየሱስን የሚያሳድዱት ሲሆን ይህ እንደሚደርስበትም ቀደም ብሎ ተተንብዮል:- “ጀርባዬን ለገራፊዎች ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ፣ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።” (ኢሳይያስ 50:6) ትንቢቱ እንደሚገልጸው መሲሑ በተቃዋሚዎች እጅ ወድቆ ሥቃይና ውርደት ይደርስበታል። ኢየሱስ ይህን በሚገባ ያውቃል። ይህ ስደት እስከ ምን ደረጃ እንደሚቀጥልም አስቀድሞ ተረድቷል። ምድራዊ ሕይወቱ የሚያበቃበት ጊዜ እየተቃረበ በሚመጣበት ጊዜም እንኳ አንዳች ፍርሃት አያድርበትም። እንደ ባልጩት የጠነከረ ቆራጥ አቋም በመያዝ ሰብዓዊ ሕይወቱ ወደሚያልፍባት የኢየሩሳሌም ከተማ ይወጣል። በመንገድ ላይ ሳሉም ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ይላቸዋል:- “እነሆ፣ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፣ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል፣ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፣ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፣ ይዘብቱበትማል ይተፉበትማል ይገርፉትማል ይገድሉትማል፣ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።” (ማርቆስ 10:33, 34) ይህ ሁሉ ግፍና በደል የሚደርስበት ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን ማስተዋል ይጠበቅባቸው በነበሩ የካህናት አለቆችና ጻፎች ዋና ቆስቋሽነት ነው።

      14, 15. ኢሳይያስ ኢየሱስ እንደሚገረፍና ውርደት እንደሚደርስበት የተናገራቸው ቃላት ፍጻሜያቸውን ያገኙት እንዴት ነው?

      14 ኒሳን 14, 33 እዘአ ምሽት ላይ ኢየሱስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ሥፍራ ሆኖ እየጸለየ ነው። ከተከታዮቹ መካከል አንዳንዶቹ አብረውት አሉ። ለዓመፅ የተነሳሱ ሰዎች በድንገት ወደ አትክልት ሥፍራው በመምጣት ኢየሱስን ያዙት። ሆኖም ኢየሱስ ይሖዋ ከእርሱ ጋር መሆኑን ያውቅ ስለነበረ በሁኔታው አልተሸበረም። አባቱን ቢለምን ከአሥራ ሁለት ጭፍሮች የሚበልጡ መላእክት በመላክ ሊያድነው እንደሚችል በመግለጽ በፍርሃት የተዋጡትን ሐዋርያቱን ካረጋጋቸው በኋላ “እንዲህ ከሆነስ . . . መጻሕፍት እንዴት ይፈጸማሉ?” አላቸው።​—⁠ማቴዎስ 26:​36, 47, 53, 54

      15 በመሲሑ ላይ የሚደርሰውን ፈተናና ሞት በተመለከተ የተነገሩት ትንቢቶች በሙሉ ተፈጽመዋል። ኢየሱስ በሳንሄድሪን ፊት ቀርቦ በሐሰት ከተወነጀለ በኋላ ጴንጤናዊው ጲላጦስ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያቀረበለት ከመሆኑም በላይ አስገርፎታል። ሮማውያን ወታደሮች “ራሱን በመቃ መቱት ተፉበትም።” በዚህ መንገድ ኢሳይያስ የተናገራቸው ቃላት ፍጻሜያቸውን አግኝተዋል። (ማርቆስ 14:​65፤ 15:​19፤ ማቴዎስ 26:​67, 68) መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ ጢም ከፍተኛ ንቀትን በሚያሳይ ሁኔታ ቃል በቃል ስለመነጨቱ የሚናገረው ነገር ባይኖርም እንኳ ኢሳይያስ በተነበየው መሠረት ይህም ድርጊት በኢየሱስ ላይ ተፈጽሞ ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለውም።c​—⁠ነህምያ 13:​25

  • “በአለቆች አትታመኑ”
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • c የሰፕቱጀንት ትርጉም ኢሳይያስ 50:​6ን “ጀርባዬን ለጅራፍ ጉንጬንም ለጥፊ አሳልፌ ሰጠሁ” ሲል ተርጉሞታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ