የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘በአንድነት ዘምሩ!’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 7. የይሖዋ ሕዝቦች ተማርከው መወሰዳቸው በይሖዋ ስም ላይ ምን አስከትሏል?

      7 ትንቢቱ እንደሚያመለክተው የይሖዋ ሕዝቦች በግዞት መኖራቸው በይሖዋ ስም ላይ የሚያስከትለው ነገር አለ:- “ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል እግዚአብሔር፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ስሜም ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ይሰደባል። ስለዚህ ወገኔ ስሜን ያውቃል፣ ስለዚህም የምናገር እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ፤ እነሆ፣ እኔ ነኝ።” (ኢሳይያስ 52:​5, 6) ይህ ሁኔታ ይሖዋን የሚመለከተው እንዴት ነው? እስራኤል በባቢሎን የባርነት ቀንበር ሥር መውደቋ እሱን ለምን ያሳስበዋል? ባቢሎን ሕዝቡን ማርካ በመውሰድ በእስራኤላውያን ላይ በድል አድራጊነት ስሜት በመፈንጠዟ እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል። እንዲህ ያለው ዕብሪት ባቢሎን የይሖዋን ስም እንድታቃልል አድርጓታል። (ሕዝቅኤል 36:​20, 21) ባቢሎን ኢየሩሳሌም ባድማ ልትሆን የቻለችው ይሖዋ በሕዝቡ ድርጊት በማዘኑ ምክንያት እንደሆነ ሳታስተውል ቀርታለች። ከዚህ ይልቅ አይሁዳውያን በባርነት ቀንበር ሥር ሊወድቁ የቻሉት አምላካቸው እነሱን ማዳን ስለተሳነው እንደሆነ አድርጋ አስባለች። እንዲያውም የባቢሎን ምክትል ገዥ የነበረው ብልጣሶር ከይሖዋ ቤተ መቅደስ የተወሰዱትን ዕቃዎች ለባቢሎን አማልክት ክብር ባዘጋጀው ግብዣ ላይ በመጠቀም በይሖዋ ላይ ተሳልቋል።​—⁠ዳንኤል 5:​1-4

  • ‘በአንድነት ዘምሩ!’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 9, 10. በዘመናችን ያሉት የአምላክ የቃል ኪዳን ሕዝቦች ይሖዋ የሚጠይቃቸውን ብቃቶችና ስሙን በተመለከተ ምን ጠለቅ ያለ ግንዛቤ አግኝተዋል?

      9 ታላቁ ቂሮስ ኢየሱስ ክርስቶስ በ1919 የአምላክን የቃል ኪዳን ሕዝብ ከታላቂቱ ባቢሎን ግዞት ነፃ ባወጣበት ጊዜ የአምላክ አገልጋዮች ይሖዋ ምን ዓይነት ብቃት እንደሚጠብቅባቸው ይበልጥ ተገነዘቡ። ከክርስትና ዘመን በፊት የነበሩ አረማውያን ያምኑባቸው የነበሩትን እንደ ሥላሴ፣ ነፍስ አትሞትም እንዲሁም በእሳታማ ሲኦል ውስጥ ለዘላለም ትሰቃያለች የሚሉትን የመሳሰሉ በርካታ የሕዝበ ክርስትና ትምህርቶች ቀደም ሲል አስወግደው ነበር። ከግዞት ነፃ ከወጡ በኋላ ደግሞ የቀሩትን የባቢሎን እምነት ርዝራዦች ጠራርገው ለማስወገድ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ ጀመሩ። በተጨማሪም ከዚህ ዓለም የፖለቲካ ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ ገለልተኛ ሆኖ የመኖርን አስፈላጊነት ተገነዘቡ። ሌላው ቀርቶ አንዳንድ ምሥክሮች ፈጽመውት ሊሆን ከሚችል ከማንኛውም በደም ባለዕዳነት ከሚያስጠይቅ ድርጊት ራሳቸውን ለማንጻት እርምጃ ወስደዋል።

      10 ከዚህም ሌላ በዘመናችን ያሉት የአምላክ አገልጋዮች በይሖዋ ስም የመጠቀምን አስፈላጊነት ይበልጥ በመገንዘባቸው ከ1931 ጀምሮ የይሖዋ ምሥክሮች በሚለው ስያሜ መጠራት ጀመሩ። በዚህ መንገድ ይሖዋንና ስሙን የሚደግፉ መሆናቸውን በይፋ አስታውቀዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከ1950 አንስቶ ባዘጋጁት የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም አማካኝነት መለኮታዊውን ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቀድሞ ወደነበረበት ትክክለኛ ቦታ መልሰዋል። በይሖዋ ስም የመጠቀምን አስፈላጊነት በመገንዘብ ስሙን እስከ ምድር ዳር ድረስ በማስታወቅ ላይ ናቸው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ