የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “እርቅ እንፍጠር”
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 5. አይሁዳውያን ያከናውኗቸው የነበሩት አንዳንዶቹ የአምልኮ ድርጊቶች ምንድን ናቸው? እነዚህ ነገሮችስ ለይሖዋ “ሸክም” የሆኑበት ለምንድን ነው?

      5 ይሖዋ ከዚህም የበለጠ ጠንከር ያለ መግለጫ መጠቀሙ ምንም አያስገርምም! “ምናምንቴውን ቁርባን ጨምራችሁ አታምጡ፤ ዕጣን በእኔ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ መባቻችሁንና ሰንበታችሁን በጉባኤም መሰብሰባችሁን አልወድድም፤ በደልንም [“ምሥጢራዊ ኃይላችሁን፣ ” NW ] የተቀደሰውንም ጉባኤ አልታገሥም። መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፣ ልታገሣቸውም ደክሜያለሁ።” (ኢሳይያስ 1:13, 14) የእህል ቁርባን፣ ዕጣን፣ ሰንበትና የተቀደሰ ጉባኤ በሙሉ አምላክ ለእስራኤል በሰጠው ሕግ ውስጥ የተጠቀሱ ነገሮች ናቸው። ሕጉ ‘መባቻን’ በሚመለከት እንዲሁ እንዲከበር ብቻ መመሪያ የሚሰጥ ቢሆንም ቀስ በቀስ በአከባበሩ ዙሪያ አንዳንድ ጤናማ ልማዶች እየዳበሩ ሄደው ነበር። (ዘኍልቁ 10:​10፤ 28:​11) መባቻው እንደ ወርኃዊ ሰንበት የሚታይ ሲሆን ሕዝቡ ከሥራው የሚያርፍበት አልፎ ተርፎም ከነቢያትና ከካህናት ለመማር አንድ ላይ የሚሰበሰብበት ዕለት ነበር። (2 ነገሥት 4:​23፤ ሕዝቅኤል 46:​3፤ አሞጽ 8:​5) እንዲህ ዓይነቶቹን በዓላት ማክበር ስህተት አልነበረውም። ስህተቱ እነዚህን በዓላት ለታይታ ብቻ ብሎ ማድረጉ ነው። ከዚህም በላይ እስራኤላውያን የአምላክን ሕግ በዘልማድ እየጠበቁ ወደ “ምሥጢራዊ ኃይሎች” ዘወር በማለት መናፍስታዊ ድርጊቶችን ጎን ለጎን ያካሂዱ ነበር።b በመሆኑም እነርሱ የሚያቀርቡት አምልኮ ለይሖዋ “ሸክም” ሆኖበት ነበር።

  • “እርቅ እንፍጠር”
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • b “ምሥጢራዊ ኃይሎች” ለሚለው ፍቺ የገባው የዕብራይስጥ ቃል “ጎጂ የሆነ” “ድብቅ ነገር” እና “የሚያምታታ” የሚልም ትርጉም አለው። ቲኦሎጂካል ዲክሽነሪ ኦቭ ዚ ኦልድ ቴስታመንት እንደሚለው ከሆነ ዕብራውያን ነቢያት “ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም ያስከተለውን ክፉ ውጤት” ለማውገዝ በዚህ ቃል ተጠቅመዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ