የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ መሲሐዊ አገልጋዩን ከፍ ከፍ ያደርገዋል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 21, 22. (ሀ) መሲሑ ለሌሎች ሲል የተሸከመው ሸክም ምንድን ነው? (ለ) ብዙዎች መሲሑን በተመለከተ ምን አመለካከት አድሮባቸዋል? በመሲሑ ላይ የደረሰው መከራ የተደመደመው እንዴት ነው?

      21 መሲሑ መሰቃየትና መሞት ያስፈለገው ለምንድን ነው? ኢሳይያስ እንዲህ ሲል ይገልጻል:- “በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ [“ተወጋ፣” አ.መ.ት ]፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፣ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።”​—⁠ኢሳይያስ 53:4-6

      22 መሲሑ የሌሎችን ደዌ ከመቀበሉም በላይ ሕመማቸውን ተሸክሟል። የእነሱን ሸክም ከላያቸው አውርዶ በራሱ ትከሻ ላይ የተሸከመ ያህል ነበር። ደዌና ሕመም ደግሞ በሰው ልጅ ኃጢአት ምክንያት የመጡ ነገሮች በመሆናቸው መሲሑ የሌሎችን ኃጢአት ተሸክሟል። ብዙዎች በኢየሱስ ላይ መከራ የደረሰበትን ምክንያት ስላልተገነዘቡ አምላክ ዘግናኝ በሆነ ደዌ በመምታት እየቀጣው እንዳለ ሆኖ ተሰምቷቸዋል።c በመሲሑ ላይ የደረሰው መከራ እየተባባሰ ሄዶ የተወጋ፣ የደቀቀና የቆሰለ ሲሆን እነዚህ ቃላት መሲሑ ከፍተኛ ሥቃይ በተሞላበት ሁኔታ መሞቱን የሚያመለክቱ ኃይለኛ መግለጫዎች ናቸው። ይሁን እንጂ የኢየሱስ ሞት ኃጢአት የማስተሰረይ ኃይል አለው። በበደላቸውና በኃጢአታቸው ጠፍተው በመቅበዝበዝ ላይ ያሉትን እንደገና በመመለስ ከአምላክ ጋር ሰላም እንዲፈጥሩ ለመርዳት የሚያስችል መሠረት ይጥላል።

  • ይሖዋ መሲሐዊ አገልጋዩን ከፍ ከፍ ያደርገዋል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 23. ኢየሱስ የሌሎችን መከራ የተሸከመው በምን መንገድ ነው?

      23 ኢየሱስ የሌሎችን መከራ የተሸከመው እንዴት ነው? የማቴዎስ ወንጌል ኢሳይያስ 53:​4ን በመጥቀስ እንዲህ ይላል:- “አጋንንት ያደረባቸውን ብዙዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ በነቢዩ በኢሳይያስ:- እርሱ ድካማችንን ተቀበለ ደዌያችንንም ተሸከመ የተባለው ይፈጸም ዘንድ፣ መናፍስትን በቃሉ አወጣ፣ የታመሙትንም ሁሉ ፈወሰ።” (ማቴዎስ 8:16, 17) ኢየሱስ ወደ እሱ የመጡትን የተለያዩ በሽታዎች ያሉባቸውን ሰዎች በመፈወስ የእነሱን መከራ ተሸክሟል። እንዲህ ያለውን ፈውስ ለመፈጸም ኃይሉን መጠቀም አስፈልጎታል። (ሉቃስ 8:​43-48) ሁሉንም ዓይነት አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ በሽታዎች መፈወስ መቻሉ የሰው ልጆችን ከኃጢአት የማንጻት ሥልጣን እንደተሰጠው የሚያረጋግጥ ነበር።​—⁠ማቴዎስ 9:​2-8

      24. (ሀ) ብዙዎች ኢየሱስ በአምላክ “እንደ ተመታ” ሆኖ የተሰማቸው ለምንድን ነው? (ለ) ኢየሱስ መከራ የደረሰበትና የሞተው ለምንድን ነው?

      24 ይሁን እንጂ ብዙዎች ኢየሱስ በአምላክ “እንደ ተመታ” ሆኖ ተሰምቷቸዋል። ምክንያቱም መከራው የደረሰበት ትልቅ ቦታ ባላቸው የሃይማኖት መሪዎች ቆስቋሽነት ነው። ይሁንና ይህ መከራ የደረሰበት እሱ በሠራው ኃጢአት ሳቢያ እንዳልሆነ አስታውስ። ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ተናግሯል:- “ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና። እርሱም ኃጢአት አላደረገም፣ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤ ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፣ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።” (1 ጴጥሮስ 2:​21, 22, 24) በአንድ ወቅት ሁላችንም በኃጢአት ምክንያት ጠፍተን ‘እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ነበር።’ (1 ጴጥሮስ 2:​25) ሆኖም ይሖዋ በኢየሱስ አማካኝነት ከኃጢአት ልንቤዥ የምንችልበትን ዝግጅት አድርጓል። በደላችንን በኢየሱስ ላይ ‘አኑሯል።’ ምንም ዓይነት ኃጢአት ያልሠራው ኢየሱስ የእኛ ኃጢአት ያስከተለውን ቅጣት በፈቃደኝነት ተቀብሏል። ባልሠራው ጥፋት እጅግ በሚያዋርድ ሁኔታ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ በመሞት ከአምላክ ጋር መታረቅ እንድንችል በር ከፍቷል።

  • ይሖዋ መሲሐዊ አገልጋዩን ከፍ ከፍ ያደርገዋል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • c “ተመታ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ከሥጋ ደዌ ጋር በተያያዘም ይሠራበታል። (2 ነገሥት 15:​5 አ.መ.ት ) ምሁራን እንደሚሉት አንዳንድ አይሁዳውያን መሲሑ በሥጋ ደዌ ይመታል የሚለውን አስተሳሰብ ያመነጩት በ⁠ኢሳይያስ 53:​4 ላይ ተመርኩዘው ነው። የባቢሎናውያን ታልሙድ ይህን ጥቅስ መሲሑን ለማመልከት የተጠቀመበት ሲሆን “በሥጋ ደዌ የተያዘው ምሁር” ሲል ጠርቶታል። ዱዌይ ቨርሽን የተባለው የካቶሊክ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በላቲኑ ቩልጌት ላይ የሰፈረውን ሐሳብ በማንጸባረቅ ይህን ጥቅስ “በሥጋ ደዌ እንደተያዘ አድርገን ቆጠርነው” ሲል ተርጉሞታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ