የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መካኗ ሴት ሐሴት ታደርጋለች
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • ‘የሴቲቱ’ ማንነት ተለይቶ ታወቀ

      3. መካኗ ‘ሴት’ ሐሴት የምታደርገው ለምንድን ነው?

      3 ምዕራፍ 54 መግቢያው ላይ የሚከተለውን አስደሳች መግለጫ ይሰጣል:- “አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፣ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፣ እልል በዪ፣ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፣ ይላል እግዚአብሔር።” (ኢሳይያስ 54:1) ኢሳይያስ ይህን ቃል ሲናገር እጅግ ተደስቶ መሆን አለበት! በተጨማሪም ይህ ቃል ፍጻሜውን ሲያገኝ በባቢሎን በግዞት የሚኖሩት አይሁዶች በእጅጉ እንደሚጽናኑ ጥርጥር የለውም! አይሁዶች በባቢሎን በግዞት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ኢየሩሳሌም ባድማ ሆና ትቆያለች። በመሆኑም ከሰብዓዊ አመለካከት አንጻር ሲታይ አንዲት መካን ሴት በስተርጅናዋ ልጅ እወልዳለሁ ብላ እንደማትጠብቅ ሁሉ ምድሪቱም እንደገና በሰው ትሞላለች ብሎ ተስፋ ማድረግ አዳጋች ነበር። ይሁን እንጂ ይህች ‘ሴት’ ወላድ የመሆን ትልቅ በረከት ይጠብቃታል። ኢየሩሳሌም እጅግ ሐሴት ታደርጋለች። እንደገና ‘በልጆች’ ወይም በነዋሪዎች ትሞላለች።

      4. (ሀ) ሐዋርያው ጳውሎስ ኢሳይያስ ምዕራፍ 54 በ537 ከዘአበ ካገኘው ፍጻሜ በላቀ ሁኔታ እንደሚፈጸም የጠቆመው እንዴት ነው? (ለ) “ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም” ማን ናት?

      4 ኢሳይያስ ላያውቀው ቢችልም የተናገረው ትንቢት ከአንድ ጊዜ በላይ ተፈጻሚነት አለው። ሐዋርያው ጳውሎስ ኢሳይያስ ምዕራፍ 54 ላይ ያለውን ሐሳብ በመጥቀስ ይህች ‘ሴት’ ከምድራዊቷ የኢየሩሳሌም ከተማ የበለጠ ነገርን እንደምታመለክት ገልጿል። “ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት” ሲል ጽፏል። (ገላትያ 4:26) “ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም” የተባለችው ማን ናት? በተስፋይቱ ምድር የምትገኘው የኢየሩሳሌም ከተማ እንደማትሆን የታወቀ ነው። ይህች ከተማ የምትገኘው ‘በላይ’ ማለትም በሰማያዊው ዓለም ሳይሆን በምድር ነው። “ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም” የአምላክ ሰማያዊት ‘ሴት’ ማለትም ኃያላን መንፈሳዊ ፍጥረታትን ያቀፈችው ድርጅቱ ነች።

      5. በ⁠ገላትያ 4:​22-31 ላይ በተገለጸው ተምሳሌታዊ ድራማ መሠረት (ሀ) አብርሃም (ለ) ሣራ (ሐ) ይስሐቅ (መ) አጋር (ሠ) እስማኤል ማንን ይወክላሉ?

      5 ይሁን እንጂ ይሖዋ ሰማያዊና ምድራዊ የሆኑ ሁለት ምሳሌያዊ ሴቶች እንዴት ሊኖሩት ይችላሉ? ይህ ሐሳብ እርስ በርሱ ይጋጫል ማለት ነውን? በፍጹም። ሐዋርያው ጳውሎስ የአብርሃም ቤተሰብ ትንቢታዊ አምሳያ ይህን ሁኔታ ግልጽ እንደሚያደርገው አመልክቷል። (ገላትያ 4:​22-31፤ በገጽ 218 ላይ የሚገኘውን “የአብርሃም ቤተሰብ​—⁠ትንቢታዊ አምሳያ” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።) የአብርሃም ሚስት የሆነችው ‘ነፃይቱ ሴት’ ሣራ መንፈሳዊ ፍጥረታትን ያቀፈችውንና በሚስት የተመሰለችውን የይሖዋን ድርጅት ትወክላለች። የአብርሃም ሁለተኛ ሚስት ወይም ቁባትና ባሪያ የሆነችው አጋር ምድራዊቷን ኢየሩሳሌም ትወክላለች።

      6. የአምላክ ሰማያዊት ድርጅት ለረጅም ጊዜ መካን ሆና የቆየችው በምን መንገድ ነው?

      6 ይህን እንደ መነሻ ይዘን በ⁠ኢሳይያስ 54:​1 ላይ የሰፈረው ሐሳብ የያዘውን ጥልቅ ትርጉም እንመረምራለን። በርከት ላሉ አሥርተ ዓመታት መካን ሆና የኖረችው ሣራ በ90 ዓመቷ ይስሐቅን ወልዳለች። በተመሳሳይም የይሖዋ ሰማያዊት ድርጅት ለረጅም ዘመን መካን ሆና ቆይታለች። ከብዙ ዘመናት በፊት ይሖዋ “ሴቲቱ” “ዘር” እንደምታፈራ በኤድን ተስፋ ሰጥቶ ነበር። (ዘፍጥረት 3:​15) ከ2, 000 ከሚበልጡ ዓመታት በኋላ ይሖዋ የተስፋውን ዘር አስመልክቶ ከአብርሃም ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። ሆኖም የአምላክ ሰማያዊት ‘ሴት’ ይህን ዘር ለማፍራት ብዙ መቶ ዘመናት መጠበቅ አስፈልጓቷል። ያም ሆኖ በአንድ ወቅት ‘መካን የነበረችው የዚህች ሴት’ ልጆች ከሥጋዊ እስራኤል ልጆች የሚበዙበት ጊዜ ደረሰ። መካን ስለሆነችው ሴት የሚገልጸው ምሳሌ መላእክት አስቀድሞ የተነገረለት ዘር የሚገለጥበትን ጊዜ ለማየት የጓጉት ለምን እንደሆነ እንድንገነዘብ ይረዳናል። (1 ጴጥሮስ 1:​12) ይህ የሆነው መቼ ነው?

      7. በ⁠ኢሳይያስ 54:​1 ላይ አስቀድሞ በተነገረው መሠረት ‘ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም’ ሐሴት ያደረገችው መቼ ነው? እንደዚያ ብለህ የመለስከውስ ለምንድን ነው?

      7 ኢየሱስ ሰው ሆኖ ሲወለድ መላእክት እጅግ እንደተደሰቱ የታወቀ ነው። (ሉቃስ 2:​9-14) ይሁን እንጂ በ⁠ኢሳይያስ 54:1 ላይ አስቀድሞ የተነገረው ክስተት ይህ አይደለም። ኢየሱስ ‘የላይኛይቱ ኢየሩሳሌም’ መንፈሳዊ ልጅ የሆነው በ29 እዘአ በመንፈስ ቅዱስ በተወለደበትና አምላክ ራሱ “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ” ብሎ በይፋ በተቀበለው ጊዜ ነው። (ማርቆስ 1:​10, 11፤ ዕብራውያን 1:​5፤ 5:​4, 5) በ⁠ኢሳይያስ 54:​1 ትንቢት ፍጻሜ መሠረት የአምላክ ሰማያዊት ‘ሴት’ ሐሴት ያደረገችው በዚያን ጊዜ ነበር። ከረጅም ዘመን ቆይታ በኋላ የተስፋውን ዘር ማለትም መሲሑን ወለደች! መካን ሆና የኖረችባቸው በርካታ መቶ ዘመናት አበቁ። ደስታዋ ግን በዚህ ብቻ የሚያበቃ አልነበረም።

      መካኗ ሴት ብዙ ልጆች ትወልዳለች

      8. የአምላክ ሰማያዊት ‘ሴት’ የተስፋውን ዘር ካፈራች በኋላም ሐሴት ያደረገችው ለምንድን ነው?

      8 ኢየሱስ ከሞተና ከተነሳ በኋላ የአምላክ ሰማያዊት ‘ሴት’ ‘ከሙታን በኩር’ የሆነውን ይህን የአምላክ ተወዳጅ ልጅ እንደገና መቀበል በመቻሏ ሐሴት አድርጋለች። (ቆላስይስ 1:​18) ከዚያ በኋላ ተጨማሪ መንፈሳዊ ልጆች ማፍራት ጀመረች። በ33 እዘአ በጰንጠቆስጤ ዕለት 120 የሚሆኑ የኢየሱስ ተከታዮች በመንፈስ ቅዱስ በመቀባት ከክርስቶስ ጋር ተባባሪ ወራሾች ሆኑ። በዚያው ዕለት ትንሽ ቆየት ብሎ ሌሎች 3, 000 የሚሆኑ ሰዎች ተጨመሩ። (ዮሐንስ 1:​12፤ ሥራ 1:​13-15፤ 2:​1-4, 41፤ ሮሜ 8:​14-16) እነዚህን ልጆች ያቀፈው ይህ ቡድን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ሄደ። የሕዝበ ክርስትና ክህደት በተስፋፋባቸው በመጀመሪያዎቹ መቶ ዘመናት ይህ እድገት በጣም አዝጋሚ ሆኖ ነበር። ይሁን እንጂ በ20ኛው መቶ ዘመን ይህ ሁኔታ ተለውጧል።

  • መካኗ ሴት ሐሴት ታደርጋለች
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • [በገጽ 220 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባ ሲሆን ኢሳይያስ 54:​1 ከዚያን ጊዜ አንስቶ የላቀ ፍጻሜውን ማግኘት ጀምሯል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ