-
መካኗ ሴት ሐሴት ታደርጋለችየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
9, 10. በጥንት ዘመን በድንኳን የምትኖር ሴት “የድንኳንሽን ሥፍራ አስፊ” የሚለው መመሪያ ምን ማድረግ ይጠይቅባት ነበር? እንዲህ ያለችው ሴት በዚህ ወቅት በጣም የምትደሰተው ለምንድን ነው?
9 ኢሳይያስ በመቀጠል አስደናቂ እድገት የሚታይበትን ጊዜ አስመልክቶ የሚከተለውን ትንቢት ተናገረ:- “የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፣ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ። በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፣ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፣ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና። አታፍሪምና አትፍሪ፤ አትዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፣ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።”—ኢሳይያስ 54:2-4
10 እዚህ ላይ ኢየሩሳሌም ልክ እንደ ሣራ በድንኳን የምትኖር ሚስትና እናት ተደርጋ ተገልጻለች። እንዲህ ያለችው እናት ቤተሰቧ እያደገ ሲሄድ መኖሪያዋን ማስፋት ይኖርባታል። የድንኳኑን ሸራና አውታሮች ማስረዘምና ካስማዎቹን አዲስ ቦታ ላይ አጥብቃ መትከል ያስፈልጋታል። ይህ ለእሷ እጅግ አስደሳች ሥራ ነው። እንዲህ በሥራ በምትወጠርበት ጊዜ የቤተሰቡ የዘር ሃረግ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ማድረግ የሚችሉ ልጆች አገኝ ይሆን እያለች ትጨነቅባቸው የነበሩትን ዓመታት በቀላሉ ልትረሳ ትችላለች።
-
-
መካኗ ሴት ሐሴት ታደርጋለችየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
a ራእይ 12:1-17 እንደሚገልጸው የአምላክ “ሴት” አንድ በጣም አስፈላጊ የሆነ “ዘር” ይኸውም አንድ መንፈሳዊ ልጅ ሳይሆን ሰማያዊውን መሲሐዊ መንግሥት በመውለድ በእጅጉ ተባርካለች። ይህን ዘር የወለደችው በ1914 ነው። (ራእይ —ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል! የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 177-86 ተመልከት።) የኢሳይያስ ትንቢት ይበልጥ የሚያተኩረው አምላክ በምድር ባሉት ቅቡዓን ልጆቿ ላይ ባፈሰሰው በረከት የተነሳ በምታገኘው ደስታ ላይ ነው።
-