-
ይሖዋ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ሰዎች መንፈስ ያነቃቃልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
6 ይሁዳ በተገኘው ሥፍራ ሁሉ ማለትም በአድባር ዛፎች ሥር፣ በሸለቆዎች፣ በተራሮችና በከተሞች ውስጥ የጣዖት አምልኮ ትፈጽማለች። ሆኖም ይሖዋ የምታደርገውን ነገር ሁሉ ይመለከት ስለነበር ብልሹ ምግባሯን በኢሳይያስ በኩል አጋልጧል:- “ከፍ ባለውም በረዘመውም ተራራ ላይ መኝታሽን አደረግሽ፣ መሥዋዕትንም ትሠዊ ዘንድ ወደዚያ ወጣሽ። ከመዝጊያውና ከመቃኑ በኋላ መታሰቢያሽን አደረግሽ።” (ኢሳይያስ 57:7-8ሀ) ይሁዳ በከፍታ ቦታዎች ላይ መንፈሳዊ ርኩሰት የምትፈጽምበትን መኝታ አዘጋጅታ ለባዕድ አማልክት መሥዋዕት ታቀርባለች።a የግል መኖሪያ ቤቶች እንኳ ሳይቀሩ ከበሮቻቸውና ከመቃኖቻቸው ጀርባ የተንጠለጠሉ ጣዖታት አሏቸው።
-
-
ይሖዋ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ሰዎች መንፈስ ያነቃቃልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
a “መኝታ” የሚለው ቃል አረማዊ አምልኮ የሚፈጸምበትን መሠዊያ አሊያም ቦታ የሚያመለክት መሆን አለበት። መኝታ ተብሎ መጠራቱ እንዲህ ያለው አምልኮ መንፈሳዊ ግልሙትና እንደሆነ እንድናስተውል ያደርገናል።
-