የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በመከራ ጊዜ በይሖዋ ታመኑ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • 5. ዛሬ ያሉት የአምላክ አገልጋዮች ከኢሳይያስ ጋር የሚመሳሰሉት በምን መንገድ ነው?

      5 ይሖዋ ለኢሳይያስ እንዲህ ብሎታል:- “አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኩሬ መስኖ ጫፍ ውጡ።” (ኢሳይያስ 7:​3) እስቲ አስበው! በዚህ ጊዜ ንጉሡ ራሱ የይሖዋን ነቢይ ሊፈልግና መመሪያ ለማግኘት ሊጥር ሲገባው ነቢዩ ንጉሡ ድረስ መሄድ አስፈልጎታል! ያም ሆኖ ግን ኢሳይያስ ይሖዋን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ነበር። በተመሳሳይም ዛሬ ያሉት የአምላክ አገልጋዮች በዚህ ዓለም ተጽእኖ ፍርሃት ላይ ወደ ወደቁት ሰዎች ይሄዳሉ። (ማቴዎስ 24:​6, 14) በየዓመቱ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ለእነዚህ የምሥራቹ ሰባኪዎች ጉብኝት ምላሽ በመስጠት በይሖዋ ላይ የሚደገፉ መሆናቸውን ማሳየታቸው እንዴት ደስ ይላል!

      6. (ሀ) ነቢዩ ለንጉሥ አካዝ ያስተላለፈው ምን የሚያበረታታ መልእክት ነው? (ለ) ዛሬ ያለው ሁኔታ ምን ዓይነት ነው?

      6 ኢሳይያስ ንጉሡ አካዝን ያገኘው ከኢየሩሳሌም ቅጥር ውጭ ሆኖ ከፊቱ ለሚጠብቀው ከበባ ለመዘጋጀት የከተማዋን የውኃ ምንጭ ሲቃኝ ነበር። ኢሳይያስ የይሖዋን መልእክት ነገረው:- “ተጠበቅ፣ ዝምም በል፤ ስለ እነዚህ ስለሚጤሱ ስለ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች [“ጉማጆች፣” የ1980 ትርጉም]፣ ስለ ሶርያና ስለ ረአሶን ስለ ሮሜልዩም ልጅ ቁጣ አትፍራ፣ ልብህም አይድከም።” (ኢሳይያስ 7:​4) ከዚህ ቀደም ብሎ ወራሪዎቹ ይሁዳን ባወደሙበት ጊዜ ቁጣቸው እንደሚፋጅ የእሳት ነበልባል ነበር። አሁን ግን ‘እንደሚጤሱ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች’ ሆነዋል። አካዝ የሶርያውን ንጉሥ ረአሶንንም ሆነ የእስራኤሉን ንጉሥ የሮሜልዩን ልጅ ፋቁሔን መፍራት አያስፈልገውም። ዛሬም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ለብዙ መቶ ዘመናት የሕዝበ ክርስትና መሪዎች በእውነተኛ ክርስቲያኖች ላይ ኃይለኛ ስደት ሲያደርሱ ኖረዋል። ይሁንና ዛሬ ሕዝበ ክርስትና በተወሰነ መጠን እንደተቃጠለ የእንጨት ጉማጅ ሆናለች። የቀራት ዕድሜም አጭር ነው።

      7. የኢሳይያስም ሆነ የልጁ ስም ለተስፋ ምክንያት የሚሆነው ለምንድን ነው?

      7 በአካዝ ዘመን የኢሳይያስ መልእክቱ ብቻ ሳይሆን የእርሱና የልጁ ስም ትርጉምም በይሖዋ ለሚታመኑ ሰዎች ተስፋ የሚሰጥ ነበር። ይሁዳ አደጋ አንዣብቦባት እንደነበር ምንም አያጠያይቅም። ሆኖም “የይሖዋ ማዳን” የሚል ትርጉም ያለው ኢሳይያስ የሚለው ስም ይሖዋ እንደሚያድናቸው የሚጠቁም ነበር። ኢሳይያስ ያሱብ የሚባለውን ወንድ ልጁን ይዞት እንዲሄድ ይሖዋ የነገረው ሲሆን የስሙም ትርጉም ‘ጥቂት ቀሪዎች ይመለሳሉ’ የሚል ነው። የይሁዳ መንግሥት በመጨረሻ ሲወድቅ እንኳ አምላክ ምሕረት በማሳየት ቀሪዎች ወደ ምድራቸው እንዲመለሱ ያደርጋል።

  • በመከራ ጊዜ በይሖዋ ታመኑ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
    • [በገጽ 103 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      ኢሳይያስ ከይሖዋ የተሰጠውን መልእክት ለአካዝ ሲያደርስ ያሱብን ይዞ ሄዷል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ