-
ይሖዋ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ሰዎች መንፈስ ያነቃቃልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
‘በሩቅም ሆነ በቅርብ ላለው ሰላም ይሁን’
22. ይሖዋ (ሀ) ንስሐ የሚገቡ ሰዎች (ለ) ክፉዎች ምን እንደሚገጥማቸው ተንብዮአል?
22 ይሖዋ ንስሐ የሚገቡ ሰዎች የሚገጥማቸውን ሁኔታ በክፉ መንገዳቸው የሚገፉ ሰዎች ከሚገጥማቸው ዕጣ ጋር በማነጻጸር እንዲህ አለ:- “የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ፤ በሩቅም በቅርብም ላለው ሰላም ሰላም ይሁን፣ እፈውሰውማለሁ፣ . . . ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፣ ውኆቹም ጭቃና ጉድፍ ያወጣሉና። ለክፉዎች ሰላም የላቸውም።”—ኢሳይያስ 57:19-21
-
-
ይሖዋ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ሰዎች መንፈስ ያነቃቃልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
23. የከንፈሮች ፍሬ የተባለው ምንድን ነው? ይሖዋ ይህን ፍሬ ‘የሚፈጥረውስ’ በምን መንገድ ነው?
23 የከንፈሮች ፍሬ የተባለው ለአምላክ የሚቀርብ የምስጋና መሥዋዕት ማለትም ለስሙ የሚደረግ ምሥክርነት ነው። (ዕብራውያን 13:15) ይሖዋ ይህን ለሰዎች የሚሰጥ ምሥክርነት ‘የሚፈጥረው’ እንዴት ነው? አንድ ሰው የምስጋና መሥዋዕት ለማቅረብ በቅድሚያ ስለ አምላክ መማርና በእርሱ ማመን ያስፈልገዋል። የአምላክ መንፈስ ፍሬ የሆነው እምነት ግለሰቡ የሰማውን ለሌሎች እንዲናገር ይገፋፋዋል። በሌላ አባባል በሕዝብ ፊት ምሥክርነት ይሰጣል። (ሮሜ 10:13-15፤ ገላትያ 5:22) በተጨማሪም አገልጋዮቹ ምስጋናውን እንዲናገሩ የሚልካቸው ይሖዋ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም። እንዲሁም ሕዝቡን ነፃ በማውጣት እንዲህ ያለ የምስጋና መሥዋዕት እንዲያቀርቡ የሚያስችላቸው ይሖዋ ነው። (1 ጴጥሮስ 2:9) በመሆኑም ይህን የከንፈሮች ፍሬ የሚፈጥረው ይሖዋ ነው ሊባል ይችላል።
24. (ሀ) የአምላክን ሰላም የሚያገኙት እነማን ናቸው? ይህስ ምን ውጤት ይኖረዋል? (ለ) የአምላክን ሰላም የማያገኙት እነማን ናቸው? ይህስ ምን ውጤት ያስከትላል?
24 አይሁዳውያን ወደ ትውልድ አገራቸው ሲመለሱ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር በመዘመር እጅግ አስደሳች የሆነ የከንፈሮች ፍሬ ያቀርባሉ። “በሩቅ” ሆነው ማለትም ከይሁዳ ርቀው ወደ ትውልድ አገራቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እየተጠባበቁም ይሁን “በቅርብ” ሆነው ማለትም በትውልድ አገራቸው የአምላክን ሰላም ማግኘታቸው ከፍተኛ ደስታ ይሰጣቸዋል። ክፉዎች የሚገጥማቸው ሁኔታ ግን ከዚህ እጅግ የተለየ ነው! የይሖዋን የቅጣት እርምጃ ተቀብለው የማይስተካከሉ በየትም ሥፍራ የሚኖሩ ክፉዎች በሙሉ ፈጽሞ ሰላም አያገኙም። እንደሚንቀሳቀስ ባሕር በመናወጥ የከንፈሮች ፍሬ ሳይሆን “ጭቃና ጉድፍ” ይኸውም ቆሻሻ የሆነ ነገር ያፈራሉ።
-
-
ይሖዋ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ሰዎች መንፈስ ያነቃቃልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
25. በሁሉም ሥፍራ የሚገኙ ሰዎች ሰላም እያገኙ ያሉት እንዴት ነው?
25 በዛሬው ጊዜም የይሖዋ አምላኪዎች የአምላክን መንግሥት ምሥራች በሁሉም ቦታ ያውጃሉ። በዓለም ዙሪያ ከ230 በሚበልጡ አገሮች የሚገኙ ክርስቲያኖች እውነተኛውን አንድ አምላክ በማወደስ የከንፈሮቻቸውን ፍሬ ያቀርባሉ። የውዳሴ መዝሙራቸው ‘ከምድር ዳርቻ’ ይሰማል። (ኢሳይያስ 42:10-12) የይሖዋ ምሥክሮች የሚያውጁትን ቃል ሰምተው አዎንታዊ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች የአምላክ ቃል የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እየተቀበሉ ነው። እነዚህ ሰዎች ‘ሰላም የሚሰጠውን አምላክ’ በማገልገል ሰላም እያገኙ ነው።—ሮሜ 16:20
-