የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ሰዎች መንፈስ ያነቃቃል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 22. ይሖዋ (ሀ) ንስሐ የሚገቡ ሰዎች (ለ) ክፉዎች ምን እንደሚገጥማቸው ተንብዮአል?

      22 ይሖዋ ንስሐ የሚገቡ ሰዎች የሚገጥማቸውን ሁኔታ በክፉ መንገዳቸው የሚገፉ ሰዎች ከሚገጥማቸው ዕጣ ጋር በማነጻጸር እንዲህ አለ:- “የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ፤ በሩቅም በቅርብም ላለው ሰላም ሰላም ይሁን፣ እፈውሰውማለሁ፣ . . . ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፣ ውኆቹም ጭቃና ጉድፍ ያወጣሉና። ለክፉዎች ሰላም የላቸውም።”​—⁠ኢሳይያስ 57:19-21

  • ይሖዋ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ሰዎች መንፈስ ያነቃቃል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 24. (ሀ) የአምላክን ሰላም የሚያገኙት እነማን ናቸው? ይህስ ምን ውጤት ይኖረዋል? (ለ) የአምላክን ሰላም የማያገኙት እነማን ናቸው? ይህስ ምን ውጤት ያስከትላል?

      24 አይሁዳውያን ወደ ትውልድ አገራቸው ሲመለሱ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር በመዘመር እጅግ አስደሳች የሆነ የከንፈሮች ፍሬ ያቀርባሉ። “በሩቅ” ሆነው ማለትም ከይሁዳ ርቀው ወደ ትውልድ አገራቸው የሚመለሱበትን ጊዜ እየተጠባበቁም ይሁን “በቅርብ” ሆነው ማለትም በትውልድ አገራቸው የአምላክን ሰላም ማግኘታቸው ከፍተኛ ደስታ ይሰጣቸዋል። ክፉዎች የሚገጥማቸው ሁኔታ ግን ከዚህ እጅግ የተለየ ነው! የይሖዋን የቅጣት እርምጃ ተቀብለው የማይስተካከሉ በየትም ሥፍራ የሚኖሩ ክፉዎች በሙሉ ፈጽሞ ሰላም አያገኙም። እንደሚንቀሳቀስ ባሕር በመናወጥ የከንፈሮች ፍሬ ሳይሆን “ጭቃና ጉድፍ” ይኸውም ቆሻሻ የሆነ ነገር ያፈራሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ