የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ግብዝነታቸው ተጋለጠ!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 17. ይሖዋ ሕዝቡ የሰንበት ሕጎችን እንዲጠብቁ የተማጸነው እንዴት ነው?

      17 የሰንበት ሕግ አምላክ ለሕዝቡ አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ ደህንነት ያለውን አሳቢነት የሚያሳይ ነው። ኢየሱስ “ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል” ሲል ተናግሯል። (ማርቆስ 2:​27) ይሖዋ የቀደሰው ይህ ቀን እስራኤላውያን ለአምላክ ያላቸውን ፍቅር ማሳየት የሚችሉበት ልዩ አጋጣሚ ፈጥሮላቸዋል። የሚያሳዝነው ግን በኢሳይያስ ዘመን ሰንበት ከንቱ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች የሚፈጸሙበትና ሰዎች የራስ ወዳድነት ፍላጎታቸውን የሚያረኩበት ዕለት ሆኖ ነበር። በመሆኑም ይሖዋ ሕዝቡን ዳግመኛ መውቀስ አስፈልጎታል። አሁንም እንደገና ልባቸውን ለመንካት በመጣር እንዲህ አለ:- “ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፣ ሰንበትንም ደስታ፣ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፣ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፣ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፣ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።”​—⁠ኢሳይያስ 58:13, 14

  • ግብዝነታቸው ተጋለጠ!
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 19. የአምላክ ሕዝቦች የሰንበትን ሕግ ካከበሩ ምን የተትረፈረፉ በረከቶች ያገኛሉ?

      19 ያም ሆኖ አይሁዳውያን ከቅጣቱ ተምረው የሰንበትን ዝግጅት ካከበሩ የተትረፈረፉ በረከቶች የማግኘት አጋጣሚ አላቸው። እውነተኛውን አምልኮ ከተከተሉና የሰንበትን ሕግ ካከበሩ በመላ ሕይወታቸው ይባረካሉ። (ዘዳግም 28:​1-13፤ መዝሙር 19:​7-11) ለምሳሌ ያህል ይሖዋ ሕዝቡን ‘በምድር ከፍታዎች ላይ ያወጣቸዋል።’ ይህ አገላለጽ ጥበቃ ማግኘትንና በጠላቶች ላይ ድል መቀዳጀትን ያመለክታል። ከፍታ ቦታዎችን ማለትም ኮረብታዎችንና ተራሮችን መቆጣጠር የቻለ ምድሩን ሁሉ መቆጣጠር ይችላል። (ዘዳግም 32:​13፤ 33:​29) እስራኤል ይሖዋን ትታዘዝ በነበረበት ዘመን ሕዝቡ የእሱን ጥበቃ ከማግኘቱም በላይ በሌሎች ብሔራት ይከበርና አልፎ ተርፎም ይፈራ ነበር። (ኢያሱ 2:​9-11፤ 1 ነገሥት 4:​20, 21) አሁንም ይሖዋን ከታዘዙ የቀድሞ ክብራቸውን መልሰው ማግኘት ይችላሉ። ይሖዋ በቀድሞ አባቶቻቸው በኩል ቃል የገባቸውን በረከቶች በተለይ ደግሞ የተስፋይቱን ምድር ቋሚ ይዞታ አድርጎ እንደሚሰጣቸው የገባውን ቃል በመፈጸም “የያዕቆብን ርስት” ሙሉ ድርሻ ይሰጣቸዋል።​—⁠መዝሙር 105:​8-11

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ