-
የይሖዋ እጅ አላጠረችምየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
17. የጽዮን ታዳጊ ማን ነው? የታደጋትስ መቼ ነው?
17 በሙሴ ሕግ መሠረት ራሱን ለባርነት የሸጠን አንድ እስራኤላዊ ሌላ ሰው ከባርነት ሊቤዠው ይችል ነበር። ቀደም ሲል በትንቢታዊው የኢሳይያስ መጽሐፍ ውስጥ ይሖዋ ንስሐ የገቡ ሰዎችን የሚታደግ አምላክ እንደሆነ ተገልጾ ነበር። (ኢሳይያስ 48:17) አሁንም በድጋሚ ንስሐ የገቡ ሰዎችን እንደሚታደግ ተገልጿል። ኢሳይያስ፣ ይሖዋ የገባውን ቃል እንዲህ ሲል ዘግቧል:- “ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፣ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፣ ይላል እግዚአብሔር።” (ኢሳይያስ 59:20) ይህ አጽናኝ ተስፋ በ537 ከዘአበ ተፈጽሟል። ይሁን እንጂ ሌላም ተፈጻሚነት አለው። ሐዋርያው ጳውሎስ እነዚህን ቃላት ከሰፕቱጀንት ትርጉም ላይ በመጥቀስ በክርስቲያኖች ላይ ፍጻሜያቸውን እንደሚያገኙ ጠቁሟል። እንዲህ ሲል ጻፈ:- “እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ:- መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል። ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።” (ሮሜ 11:26, 27) በእርግጥም ይህ የኢሳይያስ ትንቢት በዚያ ዘመን ብቻ ተወስኖ አይቀርም። ከዚህ ይልቅ እኛ ባለንበት ዘመንም ሆነ ወደፊት በስፋት ፍጻሜውን ያገኛል። እንዴት?
-
-
የይሖዋ እጅ አላጠረችምየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
19. ይሖዋ ከአምላክ እስራኤል ጋር ምን ቃል ኪዳን ገብቷል?
19 በመቀጠል ይሖዋ ከአምላክ እስራኤል ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። ዘገባው እንዲህ ይላል:- “ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል እግዚአብሔር፤ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ ከአፍህ ከዘርህም አፍ ከዘር ዘርህም አፍ አያልፍም፣ ይላል እግዚአብሔር።” (ኢሳይያስ 59:21) እነዚህ ቃላት በራሱ በኢሳይያስ ላይ ተፈጻሚነታቸውን አገኙም አላገኙ ‘ዘሩን እንደሚያይ’ ዋስትና ተሰጥቶት በነበረው በኢየሱስ ላይ ፍጻሜያቸውን እንዳገኙ ጥርጥር የለውም። (ኢሳይያስ 53:10) ኢየሱስ ከይሖዋ የተማረውን ቃል ያስተማረ ሲሆን የይሖዋ መንፈስ በላዩ ነበረ። (ዮሐንስ 1:18፤ 7:16) የአምላክ እስራኤል አባላት የሆኑትና ከእርሱ ጋር አብረው የሚወርሱት ወንድሞቹም የይሖዋን ቅዱስ መንፈስ ተቀብለው ሰማያዊ አባታቸው ያስተማራቸውን ቃል መስበካቸው የተገባ ነው። ሁሉም “ከእግዚአብሔር የተማሩ” ናቸው። (ኢሳይያስ 54:13፤ ሉቃስ 12:12፤ ሥራ 2:38) ይሖዋ በሌላ እንደማይተካቸውና ለዘላለም ምሥክሮቹ አድርጎ እንደሚጠቀምባቸው በኢሳይያስ አማካኝነት አሊያም ኢሳይያስ ትንቢታዊ አምሳያ በሆነለት በኢየሱስ በኩል ቃል ገብቷል። (ኢሳይያስ 43:10) ይሁንና በዚህ ቃል ኪዳን የሚጠቀሙት ‘ዘሮቻቸው’ እነማን ናቸው?
20. ይሖዋ ለአብርሃም የገባው ቃል በመጀመሪያው መቶ ዘመን የተፈጸመው እንዴት ነው?
20 በጥንት ዘመን ይሖዋ ለአብርሃም “የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ [“ራሳቸውን ይባርካሉ፣” NW ]” ሲል ቃል ገብቶለት ነበር። (ዘፍጥረት 22:18) በዚህ መሠረት መሲሑን የተቀበሉ ጥቂት ሥጋዊ እስራኤላውያን ቀሪዎች ወደ ብዙ አሕዛብ በመሄድ ስለ ክርስቶስ የሚናገረውን ምሥራች ሰበኩ። ከቆርኔሌዎስ አንስቶ ብዙ ያልተገረዙ አሕዛብ የአብርሃም ዘር በሆነው በኢየሱስ ‘ራሳቸውን ባርከዋል።’ የአምላክ እስራኤል አባልና የአብርሃም ዘር ሁለተኛ ክፍል ሆነዋል። እነዚህ ሰዎች የይሖዋ “ቅዱስ ሕዝብ” አካል ሲሆኑ ‘ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራቸውን የእርሱን በጎነት የመናገር’ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል።—1 ጴጥሮስ 2:9፤ ገላትያ 3:7-9, 14, 26-29
21. (ሀ) በዘመናችን የአምላክ እስራኤል አባላት ምን “ዘር” አፍርተዋል? (ለ) እነዚህ ‘ዘሮች’ ይሖዋ ከአምላክ እስራኤል ጋር በገባው ቃል ኪዳን ወይም ውል የሚበረታቱት እንዴት ነው?
21 በዛሬው ጊዜ የአምላክ እስራኤል አባላት ሙሉ በሙሉ እንደተሰበሰቡ ካሉት ሁኔታዎች በግልጽ መረዳት ይቻላል። ያም ሆኖ አሕዛብ በከፍተኛ ደረጃ እየተባረኩ ነው። እንዴት? የአምላክ እስራኤል አባላት “ዘር” ማለትም ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ያላቸውን የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በማፍራታቸው ነው። (መዝሙር 37:11, 29) እነዚህ ‘ዘሮችም’ ከይሖዋ የተማሩና በመንገዱ የሚሄዱ ናቸው። (ኢሳይያስ 2:2-4) በመንፈስ ቅዱስ የተጠመቁ ወይም የአዲሱ ቃል ኪዳን ተካፋዮች ተደርገው የማይቆጠሩ ቢሆንም እንኳ ሰይጣን የስብከት ሥራቸውን ለማደናቀፍ የሚፈጥራቸውን እንቅፋቶች ሁሉ መወጣት እንዲችሉ ይሖዋ ቅዱስ መንፈሱን በመስጠት ያጠነክራቸዋል። (ኢሳይያስ 40:28-31) እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሲሆኑ እነሱም በተራቸው የራሳቸውን ዘር እያፈሩ በሄዱ መጠን ቁጥራቸው እያደገ ይሄዳል። ይሖዋ ከቅቡዓን ክርስቲያኖች ጋር የገባው ቃል ኪዳን ወይም ውል እነዚህ ‘ዘሮች’ ይሖዋ እነሱንም ለዘላለም ቃል አቀባዮቹ አድርጎ እንደሚጠቀምባቸው እንዲተማመኑ ያደርጋቸዋል።—ራእይ 21:3, 4, 7
-