የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በብርሃኑ የሚጓዙ የሚያገኙት ደስታ
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | መጋቢት 1
    • 2 ይህንን በአእምሯችን መያዛችን ነቢዩ ኢሳይያስ የገለጸው ሁኔታ ምን ያህል ከባድ መሆኑን እንድንረዳ ያስችለናል። እርሱም “እነሆ፣ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል” ብሏል። (ኢሳይያስ 60:​2) እርግጥ ይህ ቃል በቃል ጨለማን አያመለክትም። ኢሳይያስ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ብርሃን መስጠታቸውን የሚያቆሙበት ቀን ይመጣል ማለቱ አይደለም። (መዝሙር 89:​36, 37፤ 136:​7-9) ከዚያ ይልቅ እየተናገረ ያለው ስለ መንፈሳዊ ጨለማ ነው። መንፈሳዊ ጨለማ ሞት ያስከትላል። ቃል በቃል ብርሃን ካጣን መኖር እንደማንችል ሁሉ መንፈሳዊ ብርሃን ካላገኘንም ውሎ አድሮ መሞታችን የማይቀር ነው።​—⁠ሉቃስ 1:​79

      3. ከኢሳይያስ ቃላት አንጻር ክርስቲያኖች ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?

      3 ከዚህ አንፃር ሲታይ ኢሳይያስ የተናገራቸው ቃላት በጥንቱ ይሁዳ ፍጻሜያቸውን ያገኙ ቢሆንም በጊዜያችንም ከፍተኛ ተፈጻሚነታቸውን እያገኙ በመሆኑ እነዚህን ቃላት ልብ ማለቱ ሊያሳስበን ይገባል። አዎን፣ በጊዜያችን ዓለም በመንፈሳዊ ጨለማ ተውጦ ይገኛል። እንዲህ ባለው አደገኛ ሁኔታ መንፈሳዊ ብርሃን ማግኘት ከምንም ነገር በላይ አስፈላጊ ነው። ክርስቲያኖች “ብርሃናችሁ . . . በሰው ፊት ይብራ” የሚለውን ኢየሱስ የተናገረውን ምክር መከተላቸው የተገባ የሚሆነው በዚህ ምክንያት ነው። (ማቴዎስ 5:​16) ታማኝ ክርስቲያኖች ቅን ለሆኑ ሰዎች ጨለማውን በማብራት ሕይወት የሚያገኙበትን አጋጣሚ ሊከፍቱላቸው ይችላሉ።​—⁠ዮሐንስ 8:​12

  • በብርሃኑ የሚጓዙ የሚያገኙት ደስታ
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | መጋቢት 1
    • 4. የኢሳይያስ ትንቢታዊ ቃላት የመጀመሪያ ፍጻሜያቸውን ያገኙት መቼ ነበር? በኢሳይያስ ዘመን የነበረው ሁኔታ ምን ይመስል ነበር?

      4 ኢሳይያስ ምድር በጨለማ መሸፈኗን በተመለከተ የተናገረው ትንቢት ይሁዳ በወደመችበትና ሕዝቦችዋ ወደ ባቢሎን በምርኮ በተወሰዱበት ጊዜ የመጀመሪያ ፍጻሜውን አግኝቷል። ይሁን እንጂ ከዚያን ጊዜ በፊት በራሱ በኢሳይያስ ዘመን እንኳ ሳይቀር ሕዝቡ በመንፈሳዊ ጨለማ ውስጥ ይገኝ ነበር። ኢሳይያስ “እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ኑ፣ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ” በማለት ለአገሩ ሰዎች እንዲናገር የገፋፋውም ይኸው ነው።​—⁠ኢሳይያስ 2:​5፤ 5:​20

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ