-
ብርሃን አብሪዎች የሆንነው ለምን ዓላማ ነው?መጠበቂያ ግንብ—1993 | ጥር 15
-
-
16, 17. ይሖዋ ሴት መሰል በሆነችው ድርጅቱ ላይ በ1914 ክብሩ እንዲበራ ያደረገው እንዴት ነበር? ምን ትዕዛዝስ ሰጣት?
16 ቅዱሳን ጽሑፎች መለኮታዊው ብርሃን በምድር በሙሉ የሚፈነጥቅበትን ሁኔታ ልብ ቀስቃሽ በሆነ አነጋገር ይገልጻሉ። ኢሳይያስ 60:1–3 ለይሖዋ “ሴት” ወይም ለታማኝ አገልጋዮቹ ሰማያዊት ድርጅት የተነገረ ነው። እንዲህ ይላል:- “ብርሃንሽ መጥቶአልና፣ የእግዚአብሔርም [የይሖዋም አዓት] ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፣ አብሪ። እነሆ፣ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር [ይሖዋ አዓት] ይወጣል፤ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤ አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ።”
-
-
ብርሃን አብሪዎች የሆንነው ለምን ዓላማ ነው?መጠበቂያ ግንብ—1993 | ጥር 15
-
-
18. (ሀ) በኢሳይያስ 60:2 ላይ በቅድሚያ በተነገረው መሠረት ጨለማ ምድርን የሸፈነው ለምንድን ነው? (ለ) ግለሰቦች ከምድር ጨለማ ሊወጡ የሚችሉት እንዴት ነው?
18 በተቃራኒው ግን ምድር በጨለማ አሕዛብም በድቅድቅ ጨለማ ተሸፍነዋል። ለምን? ብሔራት ሰብዓዊ አገዛዝ ይሻለናል ብለው የአምላክን ውድ ልጅ መንግሥት አንቀበልም በማለታቸው ነው። አንድን ዓይነት መስተዳድር አስወግደው በሌላ ዓይነት መስተዳድር በመተካት ችግሮቻቸውን የሚፈቱ ይመስላቸዋል። ነገር ግን ይህን ማድረጋቸው የሚጓጉለትን እፎይታ አላመጣላቸውም። በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ሆኖ ብሔራትን የሚቆጣጠረው ማን እንደሆነ መገንዘብ ተስኗቸዋል። (2 ቆሮንቶስ 4:4) የእውነተኛ ብርሃን ምንጭ የሆነውን አምላክ ባለመቀበላቸው በጨለማ ውስጥ ናቸው። (ኤፌሶን 6:12) ይሁን እንጂ ብሔራት በምንም ዓይነት መንገድ ይመላለሱ፣ ግለሰቦች ከዚህ ጨለማ ወጥተው ሊድኑ ይችላሉ። በምን መንገድ? አምላክ ባቋቋመው መንግሥት ላይ ሙሉ እምነት በመጣልና ለዚህም መንግሥት በመገዛት ነው።
19, 20. (ሀ) የይሖዋ ክብር በኢየሱስ ቅቡዓን ተከታዮች ላይ የበራው ለምንና እንዴት ነው? (ለ) ይሖዋ ቅቡዓኑን ብርሃን አብሪዎች ያደረጋቸው ለምን ዓላማ ነው? (ሐ) አስቀድሞ እንደተነገረው “ነገሥታትና” “አሕዛብ” አምላክ በሰጠን ብርሃን ተስበው የመጡት እንዴት ነው?
19 ሕዝበ ክርስትና በአምላክ መንግሥት ላይ እምነት የላትም፤ ራስዋንም ለመንግሥቱ ፈቃድ አላስገዛችም። በመንፈስ የተቀቡት የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች ግን ይህንን አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የይሖዋ መለኮታዊ ሞገስ ብርሃን በእነዚህ በሰማያዊቷ ሴት የሚታዩ ወኪሎች ላይ አብርቷል። ክብሩም በእነሱ ላይ በግልጽ ታይቷል። (ኢሳይያስ 60:19–21) በፖለቲካው ዓለም ወይም በኢኮኖሚው መድረክ የሚደርስ ማንኛውም ዓይነት ለውጥ ሊወስድባቸው የማይችል መንፈሳዊ ብርሃን በማግኘት ተደስተው ይኖራሉ። ይሖዋ ከታላቂቱ ባቢሎን ነፃ አውጥቷቸዋል። (ራእይ 18:4) የይሖዋን ተግሣጽና እርማት ስለ ተቀበሉ እንዲሁም የእርሱን ጽንፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነት በመደገፍ በታማኝነት ከጎኑ ስለቆሙ ይሖዋ በሞገሱ ይመለከታቸዋል። ከፊታቸው ብሩህ ጊዜ ይጠብቃቸዋል፤ እርሱ ባስቀመጠላቸውም ተስፋ ይደሰታሉ።
-