የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ ሕዝቡን በብርሃን ያስጌጣል
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሐምሌ 1
    • 4, 5. (ሀ) ይሖዋ ለአንዲት ሴት ምን ትእዛዝ ሰጣት? ምን ብሎስ ቃል ገባላት? (ለ) ኢሳይያስ ምዕራፍ 60 ምን ስሜት ቀስቃሽ ትንቢት ይዟል?

      4 የኢሳይያስ 60 የመጀመሪያዎቹ ቃላት አንጀት በሚበላ ሁኔታ ውስጥ ለምትገኝ አንዲት ሴት የተነገሩ ናቸው። ሴቲቱ ጨለማ ውስጥ መሬት ላይ ድፍት ብላለች። ድንገት ብርሃን ጨለማውን ሰንጥቆ ይወጣና ይሖዋ “ብርሃንሽ መጥቶአልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፣ አብሪ” ሲል ይናገራል። (ኢሳይያስ 60:​1) ሴቲቱ ተነስታ የምትቆምበትና የአምላክን ብርሃን ማለትም ክብሩን የምታንጸባርቅበት ጊዜ ደርሷል። እንዴት? ቀጥሎ ባለው ቁጥር መልሱን እናገኛለን:- “እነሆ፣ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል።” (ኢሳይያስ 60:​2) ሴቲቱ ይሖዋ እንዳዘዛት ስታደርግ አስደናቂ ውጤት እንደምታገኝ ተነግሯታል። ይሖዋ “አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ” ብሏታል።​—⁠ኢሳይያስ 60:​3

      5 በእነዚህ ሦስት ቁጥሮች ላይ የሚገኙት ስሜት ቀስቃሽ ቃላት የኢሳይያስ ምዕራፍ 60 መግቢያ ከመሆናቸውም በተጨማሪ ቀሪው ክፍል ምን እንደያዘ ጠቅለል አድርገው ይገልጻሉ። ይህ ምዕራፍ በትንቢቱ ውስጥ የተገለጸችው ሴት ያጋጠማትን ሁኔታ እንዲሁም የሰው ዘር በጨለማ ቢዋጥም በይሖዋ ብርሃን እንዴት መኖር እንደምንችል ይጠቁመናል። ይሁንና በእነዚህ ሦስት ቁጥሮች ውስጥ የተሰጠው ትንቢታዊ መግለጫ ትክክለኛ ትርጉም ምንድን ነው?

      6. በኢሳይያስ ምዕራፍ 60 ላይ የተጠቀሰችው ሴት ማን ናት? በምድር ላይ የምትወከለውስ በማን ነው?

      6 በኢሳይያስ 60:​1-3 ላይ የተጠቀሰችው ሴት መንፈሳዊ ፍጥረታትን ያቀፈችው የይሖዋ ሰማያዊ ድርጅት ጽዮን ናት። በዛሬው ጊዜ ጽዮን በምድር ላይ የምትወከለው ‘በአምላክ እስራኤል’ ቀሪዎች ማለትም ከክርስቶስ ጋር በሰማይ የመግዛት መብት ያላቸውን በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖች ባቀፈው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ነው። (ገላትያ 6:​16) ይህ መንፈሳዊ ብሔር በአጠቃላይ 144, 000 አባላት ያሉት ሲሆን የኢሳይያስ ምዕራፍ 60 ዘመናዊ ፍጻሜ “በመጨረሻው ቀን” በምድር ላይ በሚኖሩት የዚህ ብሔር አባላት ላይ ያተኩራል። (2 ጢሞቴዎስ 3:​1፤ ራእይ 14:​1) ትንቢቱ የእነዚህ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ተባባሪዎችና “የሌሎች በጎች” ክፍል ስለሆኑት ስለ ‘እጅግ ብዙ ሰዎችም’ ብዙ ሐሳብ ይዟል።​—⁠ራእይ 7:​9፤ ዮሐንስ 10:​16

  • ይሖዋ ሕዝቡን በብርሃን ያስጌጣል
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሐምሌ 1
    • 8. በ1919 የተከናወነው አስገራሚ ለውጥ ምንድን ነው? ምንስ ውጤት አስገኝቷል?

      8 ይሁን እንጂ በ1919 አንድ አስገራሚ ለውጥ ተከናወነ። ይሖዋ በጽዮን ላይ ብርሃን አበራ! በሕይወት የነበሩት የአምላክ እስራኤል አባላት የምሥራቹን ዳግም ያለ ፍርሃት በማወጅ የአምላክን ብርሃን ለማንጸባረቅ ተንቀሳቀሱ። (ማቴዎስ 5:​14-16) የእነዚህ ክርስቲያኖች ቅንዓት ዳግመኛ በመቀጣጠሉ ምክንያት ሌሎችም ወደ ይሖዋ ብርሃን ሊሳቡ ችለዋል። በመጀመሪያ ወደ ብርሃኑ ተስበው የመጡት የአምላክ እስራኤል ተጨማሪ አባላት በመሆን በመንፈስ ተቀብተዋል። እነዚህ ቅቡዓን ከክርስቶስ ጋር በአምላክ ሰማያዊ መንግሥት ተባባሪ ገዥዎች ስለሚሆኑ ኢሳይያስ 60:​3 ላይ ነገሥታት ተብለው ተጠርተዋል። (ራእይ 20:​6) ከጊዜ በኋላ ደግሞ የሌሎች በጎች ክፍል የሆኑት እጅግ ብዙ ሰዎች ወደ ይሖዋ ብርሃን ተስበዋል። በትንቢቱ ውስጥ የተጠቀሱት “አሕዛብ” እነርሱ ናቸው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ