የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የስብከቱ ሥራ ያስገኘው ውጤት—‘አዝመራው ነጥቷል’
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
    • 15. በኢሳይያስ 60:5, 22 ላይ የሚገኘው ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? (በገጽ 93 ላይ የሚገኘውን “ይሖዋ እንዲቻል አድርጓል” የሚለውን ሣጥን እና ከገጽ 96-97 ላይ የሚገኘውን “‘ትንሽ የሆነው፣ ኃያል ብሔር’ የሆነው እንዴት ነው?” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።)

      15 ኢየሱስ እነዚህን ምሳሌዎች ከመናገሩ ከ800 ዓመታት በፊት ይሖዋ፣ በዘመናችን የሚከናወነው መንፈሳዊ የመከር ሥራ ምን ያህል ስፋት እንደሚኖረው እንዲሁም ይህ የመከር ሥራ ደስታ እንደሚያስገኝ በነቢዩ ኢሳይያስ አማካኝነት በማይረሳ መልኩ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር።c ይሖዋ፣ ሰዎች “ከሩቅ” አካባቢዎች ወደ ድርጅቱ እንደሚጎርፉ ገልጿል። በዛሬው ጊዜ ምድር ላይ ያሉትን ቅቡዓን ቀሪዎች በአንዲት ሴት በመመሰል ይሖዋ እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ “ታያለሽ፤ ፊትሽም ይፈካል፤ ልብሽ በኃይል ይመታል፤ በደስታም ይሞላል፤ ምክንያቱም የባሕር ብልጽግና ወደ አንቺ ይጎርፋል፤ የብሔራትም ሀብት ወደ አንቺ ይመጣል።” (ኢሳ. 60:1, 4, 5, 9) በእርግጥም ይህ ትንቢት በትክክል ተፈጽሟል! በዛሬው ጊዜም ይሖዋን ለብዙ ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩ አገልጋዮቹ፣ ባሉበት አገር ውስጥ የነበሩት ጥቂት የመንግሥቱ አስፋፊዎች ቁጥራቸው ጨምሮ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ መሆናቸውን ሲመለከቱ ልባቸው በደስታ ይሞላል።

  • የስብከቱ ሥራ ያስገኘው ውጤት—‘አዝመራው ነጥቷል’
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
    • c ይህን አስገራሚ ትንቢት በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን፣ ጥራዝ 2 የተባለውን መጽሐፍ ከገጽ 303-320 ተመልከት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ