-
እውነተኛው አምልኮ በዓለም ዙሪያ ይስፋፋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
13. በዘመናችን ‘ወንዶቹና ሴቶቹ ልጆች’ እነማን ናቸው? ‘የአሕዛብ ብልጥግና’ የተባሉትስ እነማን ናቸው?
13 ኢሳይያስ 60:4-9 ላይ የሰፈረው ዘገባ የይሖዋ ‘ሴት’ ጨለማ በዋጠው በዚህ ዓለም ውስጥ ብርሃን ከፈነጠቀችበት ጊዜ አንስቶ በዓለም ዙሪያ የተገኘውን ጭማሪ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሕያው መግለጫ ነው! በመጀመሪያ የተሰበሰቡት ቅቡዓን ክርስቲያኖች የሆኑት የሰማያዊቷ ጽዮን “ወንዶች ልጆች” እና “ሴቶች ልጆች” ናቸው። እነዚህ ክርስቲያኖች በ1931 የይሖዋ ምሥክሮች መሆናቸውን በይፋ አሳውቀዋል። ከዚያም ‘የአሕዛብ ብልጥግና’ እና “የባሕሩ በረከት” ማለትም እንደ ደመና ያሉ በርካታ ቅን ሰዎች በከፍተኛ ፍጥነት ከቀሪዎቹ የክርስቶስ ወንድሞች ጋር ተቀላቅለዋል።b በዛሬው ጊዜ ከአራቱም የምድር ማዕዘናትና ከሁሉም የኑሮ ደረጃዎች የተውጣጡት እነዚህ አገልጋዮች ከአምላክ እስራኤል ጎን በመሰለፍ ሉዓላዊ ጌታቸውን ይሖዋን እያወደሱ ከመሆኑም በላይ በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ከሁሉ የላቀ ታላቅ ስም ያለው መሆኑን በማስታወቅ ስሙን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ናቸው።
-
-
እውነተኛው አምልኮ በዓለም ዙሪያ ይስፋፋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
b ከ1930 በፊትም ከአምላክ እስራኤል ጋር የተባበሩ ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ቀናተኛ ክርስቲያኖች የነበሩ ቢሆንም ቁጥራቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣው ከ1930ዎቹ ዓመታት ወዲህ ነው።
-