-
በመከራ ጊዜ በይሖዋ ታመኑየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
9. ለአካዝም ሆነ ዛሬ ላሉት ክርስቲያኖች ድፍረት ሊሰጣቸው የሚገባው የትኛው ማረጋገጫ ነው?
9 ሶርያና እስራኤል የዶለቱት ነገር ይሳካላቸው ይሆን? አይሳካላቸውም። ይሖዋ “ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም” ሲል ተናግሯል። (ኢሳይያስ 7:7) ይሖዋ በኢሳይያስ አማካኝነት፣ በኢየሩሳሌም ላይ የታቀደው ከበባ እንደሚከሽፍ ብቻ ሳይሆን “በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ ኤፍሬም ይሰባበራልና ሕዝብ አይሆንም” ሲልም ተናግሯል። (ኢሳይያስ 7:8) አዎን፣ በ65 ዓመታት ውስጥ እስራኤል ሕዝብ መሆኗ ያከትማል።a ቁርጥ ያለ ጊዜ ተጠቅሶ የተሰጠው ይህ ዋስትና አካዝን ሊያበረታው ይገባል። በተመሳሳይም ዛሬ ያሉት የአምላክ ሕዝቦች የሰይጣን ዓለም የቀረው ጊዜ እየተሟጠጠ መሆኑን በማወቃቸው ይበረታታሉ።
-
-
በመከራ ጊዜ በይሖዋ ታመኑየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
-
-
a ይህ ትንቢት ፍጻሜውን ስለሚያገኝበት መንገድ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ኒው ዮርክ በሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር የተዘጋጀውን ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ጥራዝ 1 ገጽ 62 እና 758 ተመልከት።
-