-
እውነተኛው አምልኮ በዓለም ዙሪያ ይስፋፋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
11, 12. (ሀ) ‘ሴቲቱ’ በስተምዕራብ በኩል ዓይኗን ስታቀና ምን ትመለከታለች? (ለ) ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች እየተቻኮሉ ወደ ኢየሩሳሌም በመምጣት ላይ ያሉት ለምንድን ነው?
11 ቀጥሎ ደግሞ ይሖዋ ‘ሴቲቱ’ በስተምዕራብ ወዳለው አድማስ እንድትመለከት ካደረገ በኋላ “ርግቦች ወደ ቤታቸው እንደሚበርሩ፣ እነዚህ እንደ ደመና የሚበርሩ እነማን ናቸው?” የሚል ጥያቄ አቀረበ። ይሖዋ ራሱ እንዲህ በማለት መልስ ሰጠ:- “እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለእግዚአብሔር ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመጡ ዘንድ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።”—ኢሳይያስ 60:8, 9
12 ‘ከሴቲቱ’ ጋር አብረህ ቆመህ በስተምዕራብ በኩል ከታላቁ ባሕር ባሻገር እየተመለከትክ እንዳለህ አድርገህ አስብ። ምን ታያለህ? እንደ ደመና ያሉ ነጫጭ ነቁጦች በባሕሩ ላይ እየተንሳሰፉ ሲተሙ ከሩቅ ይታያሉ። ከሩቅ ሲታዩ ርግቦች ቢመስሉም እንኳ እየቀረቡ ሲመጡ ሸራቸውን የዘረጉ መርከቦች እንደሆኑ ትገነዘባለህ። “ከሩቅ” የመጡ ናቸው።a (ኢሳይያስ 49:12) መርከቦቹ በጣም ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ በከፍተኛ ፍጥነት እየቀዘፉ ወደ ጽዮን ሲመጡ ወደ ቤታቸው የሚበርሩ ርግቦች ይመስላሉ። መርከቦቹ ይህን ያህል የተጣደፉት ለምንድን ነው? ርቀው ከሚገኙ ወደቦች የጫኗቸውን የይሖዋን አምላኪዎች ለማድረስ ስለጓጉ ነው። ከምሥራቅም ሆነ ከምዕራብ እንዲሁም ከሩቅም ሆነ ከቅርብ በመምጣት ላይ ያሉት እስራኤላውያንና የባዕድ አገር ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ራሳቸውንም ሆነ ያላቸውን ነገር ሁሉ ለአምላካቸው ለይሖዋ ስም ለማዋል እየተጣደፉ ነው።—ኢሳይያስ 55:5
-
-
እውነተኛው አምልኮ በዓለም ዙሪያ ይስፋፋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
a ተርሴስ በዛሬው ጊዜ ስፔይን በመባል በሚታወቀው የምድር ክፍል ትገኝ እንደነበር ይታመናል። ይሁንና አንዳንድ የማመሳከሪያ ጽሑፎች እንደሚሉት “የተርሴስ መርከቦች” የሚለው አገላለጽ የመርከቦቹን ዓይነት ማለትም “ወደ ተርሴስ ለመጓዝ አመቺ” የሆኑትን በሌላ አባባል ርቀው ወደሚገኙ ወደቦች ረጅም ጉዞ ለማድረግ ተስማሚ የሆኑትን “ረጃጅም ተራዳ ያላቸው በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ መርከቦች” ያመለክታል።—1 ነገሥት 22:48
-