-
መንፈሳዊውን ገነት ይበልጥ አስውቡትመጠበቂያ ግንብ—2015 | ሐምሌ 15
-
-
1, 2. በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ “የእግር ማሳረፊያ” የሚለው አገላለጽ ምንን ለማመልከት አገልግሏል?
ይሖዋ አምላክ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድር ደግሞ የእግሬ ማሳረፊያ ናት” ብሏል፤ እንዲህ ማለቱም የተገባ ነው። (ኢሳ. 66:1) ‘የእግሩን ማሳረፊያ’ አስመልክቶ ደግሞ “እግሬ የሚያርፍበትንም ስፍራ አከብራለሁ” ብሏል። (ኢሳ. 60:13) ይህን የሚያደርገው እንዴት ነው? ደግሞስ የምንኖረው አምላክ “የእግሬ ማሳረፊያ” ብሎ በጠራው ቦታ ከመሆኑ አንጻር ይህ ጥቅስ ለእኛ ምን ትርጉም አለው?
2 “የእግር ማሳረፊያ” የሚለው አገላለጽ ከምድርም በተጨማሪ እስራኤላውያን ይጠቀሙበት የነበረውን የጥንቱን ቤተ መቅደስ ለማመልከት በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ በምሳሌያዊ መንገድ ተሠርቶበታል። (1 ዜና 28:2፤ መዝ. 132:7) በምድር ላይ የነበረው ይህ ቤተ መቅደስ የእውነተኛው አምልኮ ማዕከል ሆኖ አገልግሏል። በዚህ ምክንያት ይህ ቤተ መቅደስ በአምላክ ዓይን እጅግ ውብ ነበር፤ እንዲሁም ቤተ መቅደሱ መኖሩ በራሱ የይሖዋ እግር የሚያርፍበትን ቦታ ያስከብር ነበር።
3. ታላቁ የአምላክ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ምንድን ነው? የተቋቋመውስ መቼ ነው?
3 በዛሬው ጊዜ የእውነተኛው አምልኮ ማዕከል በምድር ላይ የሚገኝ ቤተ መቅደስ መሆኑ ቀርቷል። ያም ቢሆን ከማንኛውም ሕንፃ ይበልጥ ይሖዋን የሚያስከብር መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ አለ። ይህ ቤተ መቅደስ በኢየሱስ ክርስቶስ ክህነትና መሥዋዕት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ለመታረቅ የሚያስችለውን ዝግጅት ያመለክታል። ቤተ መቅደሱ የተቋቋመው ኢየሱስ በ29 ዓ.ም. ሲጠመቅ ማለትም የይሖዋ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሊቀ ካህናት ሆኖ ሲቀባ ነው።—ዕብ. 9:11, 12
4, 5. (ሀ) መዝሙር 99 የይሖዋ እውነተኛ አምላኪዎች ምን ልባዊ ፍላጎት እንዳላቸው ይገልጻል? (ለ) ራሳችንን ምን ብለን መጠየቅ ይኖርብናል?
4 እኛም ለመንፈሳዊው ቤተ መቅደስ ያለንን አድናቆት መግለጽ ስለምንፈልግ የይሖዋን ስም በማሳወቅ እሱን እናወድሰዋለን፤ እንዲሁም በምሕረት ተነሳስቶ የቤዛ ዝግጅት ስላደረገልን ከፍ ከፍ እናደርገዋለን። በዛሬው ጊዜ ከስምንት ሚሊዮን የሚበልጡ እውነተኛ ክርስቲያኖች ይሖዋን እያከበሩት መሆኑ ምንኛ የሚያስደስት ነው! ምድርን ለቀው ወደ ሰማይ ከሄዱ በኋላ አምላክን እንደሚያወድሱ አድርገው በተሳሳተ መንገድ ከሚያስቡ አንዳንድ ሃይማኖተኛ ሰዎች በተቃራኒ ሁሉም የይሖዋ ምሥክሮች በአሁኑ ወቅት እዚሁ ምድር ላይ አምላክን የማመስገንን አስፈላጊነት ተገንዝበዋል።
5 እንዲህ በማድረግ በመዝሙር 99:1-3, 5 ላይ የተገለጹትን የይሖዋን ታማኝ አገልጋዮች ምሳሌ እንከተላለን። (ጥቅሱን አንብብ።) ይህ መዝሙር እንደሚጠቁመው ሙሴ፣ አሮንና ሳሙኤል በዘመናቸው የነበረውን የእውነተኛ አምልኮ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ደግፈዋል። (መዝ. 99:6, 7) በዛሬው ጊዜም በምድር ያሉት የኢየሱስ ቅቡዓን ወንድሞች በሰማይ ከእሱ ጋር ካህናት ሆነው ለማገልገል ከመሄዳቸው በፊት በመንፈሳዊው ቤተ መቅደስ ምድራዊ አደባባይ በታማኝነት እያገለገሉ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩት “ሌሎች በጎች” በታማኝነት ይደግፏቸዋል። (ዮሐ. 10:16) ቅቡዓንና ሌሎች በጎች ያላቸው ተስፋ የተለያየ ቢሆንም የአምላክ የእግር ማሳረፊያ በሆነችው በምድር ላይ ሁለቱም ቡድኖች ይሖዋን በአንድነት እያመለኩ ነው። ይሁንና ‘ይሖዋ ለንጹሕ አምልኮ ያደረገውን ዝግጅት በተሟላ ሁኔታ እየደገፍኩ ነው?’ ብለን ራሳችንን መጠየቃችን የተገባ ነው።
-
-
መንፈሳዊውን ገነት ይበልጥ አስውቡትመጠበቂያ ግንብ—2015 | ሐምሌ 15
-
-
7 የይሖዋን ሞገስ ያገኙትና በመንፈሳዊው ቤተ መቅደሱ እያገለገሉ ያሉት እነማን እንደሆኑ በ1919 በግልጽ ታወቀ። እነዚህ ክርስቲያኖች ለአምላክ የሚያቀርቡት አገልግሎት በእሱ ዘንድ ይበልጥ ተቀባይነት እንዲኖረው በመንፈሳዊ ሁኔታ ነጽተዋል። (ኢሳ. 4:2, 3፤ ሚል. 3:1-4) ሐዋርያው ጳውሎስ ከበርካታ ዘመናት በፊት የተመለከተው ራእይ በዚህ ጊዜ በተወሰነ መንገድ ፍጻሜ ማግኘት ጀመረ።
8, 9. ጳውሎስ በራእይ የተመለከተውን “ገነት” ሦስት ገጽታዎች አብራራ።
8 ጳውሎስ የተመለከተው ራእይ በ2 ቆሮንቶስ 12:1-4 ላይ ተመዝግቦ ይገኛል። (ጥቅሱን አንብብ።) ጳውሎስ የተመለከተውን ተአምራዊ ራእይ፣ የተገለጠ መልእክት በማለትም ገልጾታል። የተመለከተው ነገር በእሱ ዘመን የነበረ ሳይሆን ወደፊት የሚፈጸም ነው። ጳውሎስ “ወደ ሦስተኛው ሰማይ [ሲነጠቅ]” የተመለከተው “ገነት” ምንድን ነው? ቃል በቃል በምድር ላይ፣ በመንፈሳዊ ሁኔታ እንዲሁም በሰማይ የሚኖረውን ገነት ያመለክታል፤ ወደፊት ሦስቱም ነገሮች በአንድ ወቅት ላይ ይኖራሉ። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም “ገነት” የሚለው ቃል ወደፊት በምድር ላይ ቃል በቃል የሚኖረውን ገነት ሊጠቁም ይችላል። (ሉቃስ 23:43) ከዚህም ሌላ በአዲሱ ዓለም ውስጥ በተሟላ ሁኔታ የሚኖረውን መንፈሳዊ ገነትም ሊያመለክት ይችላል። በተጨማሪም ‘የአምላክን ገነት’ ይኸውም ይሖዋ በሚኖርበት በሰማይ የመሆንን አስደናቂ መብት ሊያመለክት ይችላል።—ራእይ 2:7
9 ይሁንና ጳውሎስ “በአንደበት ሊገለጹ የማይችሉና ሰው እንዲናገራቸው ያልተፈቀዱ ቃላት [እንደሰማ]” የገለጸው ለምንድን ነው? ጳውሎስ ይህን የተናገረው በዚህ ራእይ ላይ የተመለከታቸውን አስደናቂ ነገሮች በዝርዝር የሚያብራራበት ጊዜ ስላልደረሰ ነው። ዛሬ ግን የአምላክ ሕዝቦች ስላገኟቸው በረከቶች መናገር ተፈቅዷል።
10. “መንፈሳዊ ገነት” እና “መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ” የሚሉት አገላለጾች ተመሳሳይ ነገር አያመለክቱም የምንለው ለምንድን ነው?
10 “መንፈሳዊ ገነት” የሚለው ሐሳብ ከምንጠቀምባቸው ቲኦክራሲያዊ አገላለጾች አንዱ ሆኗል። ይህ አገላለጽ ከአምላክና ከወንድሞቻችን ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን የሚያደርገውን ልዩ የሆነና በመንፈሳዊ የበለጸገ ሁኔታ ያመለክታል። እርግጥ ነው፣ “መንፈሳዊ ገነት” እና “መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ” የሚሉት ሐሳቦች አንድ እንደሆኑ አድርገን ልንደመድም አይገባም። መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ የሚባለው አምላክ ከእውነተኛው አምልኮ ጋር በተያያዘ ያደረገው ዝግጅት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ መንፈሳዊው ገነት አምላክ ሞገሱን የሚያሳያቸውን እንዲሁም በመንፈሳዊው ቤተ መቅደሱ እሱን የሚያገለግሉትን ሰዎች በግልጽ ለመለየት ይረዳል።—ሚል. 3:18
11. ከመንፈሳዊው ገነት ጋር በተያያዘ በዛሬው ጊዜ ምን መብት አለን?
11 ከ1919 ጀምሮ ይሖዋ ፍጽምና የጎደላቸው ሰዎች በምድር ላይ ያለውን መንፈሳዊ ገነት በማልማት፣ በማጠናከርና በማስፋፋት ከእሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ መፍቀዱን ማወቃችን ምንኛ የሚያስደስት ነው! በዚህ አስደናቂ ሥራ የበኩልህን ድርሻ እያበረከትክ እንዳለ ይሰማሃል? እንዲሁም የይሖዋን ‘የእግር ማሳረፊያ’ በማስከበር ረገድ ከእሱ ጋር አብረህ መሥራትህን ለመቀጠል ትነሳሳለህ?
-