የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • እውነተኛው አምልኮ በዓለም ዙሪያ ይስፋፋል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 29, 30. “ታናሹ ለሺህ” የሆነው እንዴት ነው?

      29 በ⁠ኢሳይያስ ምዕራፍ 60 መደምደሚያ ላይ ይሖዋ በራሱ ስም ዋስትና የሰጠበትን የማይታጠፍ ቃል እናገኛለን። እንዲህ አለ:- “ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሹ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር በዘመኑ ይህን አፋጥነዋለሁ።” (ኢሳይያስ 60:​22) ተበታትነው የነበሩት ቅቡዓን ክርስቲያኖች በ1919 እንደገና ተሰባስበው ሥራቸውን ማከናወን ሲጀምሩ ‘አነስተኛ’ ነበሩ።e የተቀሩት መንፈሳዊ እስራኤላውያን ሲሰበሰቡ ግን ቁጥራቸው በከፍተኛ ደረጃ ጨመረ። እጅግ ብዙ ሰዎች መሰብሰብ ሲጀምሩ ደግሞ ቁጥራቸው በሚያስደንቅ ሁኔታ እየጨመረ ሄደ።

      30 ብዙም ሳይቆይ በአምላክ ሕዝብ መካከል ያለው ሰላምና ጽድቅ ቅን ልብ ያላቸውን በርካታ ሰዎች በመሳቡ ቃል በቃል “ታናሹ” “ብርቱ ሕዝብ” ሆነ። በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው በዓለም ላይ ካሉት በርካታ ሉዓላዊ መንግሥታት የሕዝብ ቁጥር ይበልጣል። ይሖዋ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የመንግሥቱን ሥራ ከመምራቱም በላይ በእጅጉ እንዳፋጠነው በግልጽ መረዳት ይቻላል። እውነተኛው አምልኮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲስፋፋ ማየትና የዚህ እድገት አካል መሆን መቻል ምንኛ የሚያስደስት ነው! አዎን፣ ይህ ጭማሪ እነዚህን ትንቢቶች ከረጅም ጊዜ በፊት የተናገረውን አምላክ ይሖዋን እንደሚያስከብረው ማወቃችን በእጅጉ ያስደስተናል።

  • እውነተኛው አምልኮ በዓለም ዙሪያ ይስፋፋል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • e በ1918 ቃሉን በመስበኩ ሥራ በየወሩ ይካፈሉ የነበሩት ሰዎች አማካይ ቁጥር ከ4, 000 አይበልጥም ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ