-
በዛሬው ጊዜ ሰባቱ እረኞችና ስምንቱ አለቆች እነማን ናቸው?መጠበቂያ ግንብ—2013 | ኅዳር 15
-
-
3 ኢሳይያስ እንዲህ አለ፦ “እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። . . . ሕፃኑ ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት [የሶርያና የእስራኤል] ምድር ባድማ ይሆናል።” (ኢሳ. 7:14, 16) የዚህ ትንቢት የመጀመሪያው ክፍል አብዛኛውን ጊዜ ከመሲሑ መወለድ ጋር ተያይዞ ይገለጻል፤ ደግሞም ትክክል ነው። (ማቴ. 1:23) ይሁን እንጂ “ሁለቱ ነገሥታት” ማለትም የሶርያ ንጉሥና የእስራኤል ንጉሥ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. በይሁዳ ላይ የፈጠሩት ስጋት አልነበረም፤ በመሆኑም ስለ አማኑኤል የሚናገረው ትንቢት የመጀመሪያውን ፍጻሜ በኢሳይያስ ዘመን አግኝቶ መሆን አለበት።
4 ኢሳይያስ ይህን አስገራሚ ትንቢት ከተናገረ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሚስቱ ፀነሰችና ማኸር ሻላል ሃሽ ባዝ የተባለ ወንድ ልጅ ወለደችለት። ይህ ልጅ ኢሳይያስ የተናገረለት “አማኑኤል” ሊሆን ይችላል።a በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን አንድ ልጅ ሲወለድ አንድን ለየት ያለ ክስተት ለመዘከር የሚያስችል ስም ሊወጣለት ይችላል፤ ሆኖም ወላጆቹና ዘመዶቹ የሚጠሩት በሌላ ስም ይሆናል። (2 ሳሙ. 12:24, 25) ኢየሱስ፣ አማኑኤል በሚለው ስም ተጠርቶ እንደሚያውቅ የሚያሳይ አንድም ማስረጃ የለም።—ኢሳይያስ 7:14ን እና 8:3, 4ን አንብብ።
-
-
በዛሬው ጊዜ ሰባቱ እረኞችና ስምንቱ አለቆች እነማን ናቸው?መጠበቂያ ግንብ—2013 | ኅዳር 15
-
-
a በኢሳይያስ 7:14 ላይ “ድንግል” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጡ ቃል ያገባችንም ሴት ሊያመለክት ይችላል። በመሆኑም ይህ ቃል የኢሳይያስን ሚስትም ሆነ አይሁዳዊቷን ድንግል ማርያምን ሊያመለክት ይችላል።
-