የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በጽዮን ጽድቅ ይበቅላል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 17. (ሀ) የአምላክ እስራኤል አባላት ምን ይባላሉ? (ለ) የኃጢአት ይቅርታ ለማግኘት የሚያስፈልገው ብቸኛው መሥዋዕት የትኛው ነው?

      17 ስለ አምላክ እስራኤልስ ምን የተገለጸ ነገር አለ? ይሖዋ በኢሳይያስ በኩል እንዲህ ይላቸዋል:- “እናንተ ግን የእግዚአብሔር ካህናት ትባላላችሁ፣ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሩአችኋል፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፣ በክብራቸውም ትመካላችሁ።” (ኢሳይያስ 61:6) በጥንቷ እስራኤል ይሖዋ ለሕዝቡም ሆነ ለራሳቸው መሥዋዕት የሚያቀርቡ ሌዋውያን ካህናትን ይሾም ነበር። ይሁን እንጂ በ33 እዘአ ይሖዋ በሌዋውያን የክህነት አገልግሎት መጠቀሙን በመተው ሌላ የተሻለ ዝግጅት እንዲቋቋም አደረገ። ፍጹሙን የኢየሱስ ሕይወት ለሰው ልጆች ኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ ተቀበለ። የኢየሱስ መሥዋዕት ለሁልጊዜ የሚያገለግል በመሆኑ ከዚያን ጊዜ ወዲህ ሌላ ተጨማሪ መሥዋዕት ማቅረብ አላስፈለገም።​—⁠ዮሐንስ 14:​6፤ ቆላስይስ 2:​13, 14፤ ዕብራውያን 9:​11-14, 24

      18. የአምላክ እስራኤል አባላት ምን ዓይነት ካህናት ሆነዋል? ተልዕኳቸውስ ምንድን ነው?

      18 ታዲያ የአምላክ እስራኤል አባላት “የእግዚአብሔር ካህናት” የሆኑት እንዴት ነው? ሐዋርያው ጴጥሮስ እንደ እሱው ላሉ ቅቡዓን ክርስቲያኖች እንዲህ ሲል ጽፏል:- “እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትነግሩ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ።” (1 ጴጥሮስ 2:9) በመሆኑም ቅቡዓን ክርስቲያኖች በቡድን ደረጃ አንድ ልዩ ተልዕኮ የተሰጣቸው ካህናት ሆነዋል። የይሖዋን ክብር ለአሕዛብ በመናገር ምሥክሮቹ ሆነው ያገለግላሉ። (ኢሳይያስ 43:​10-12) ቅቡዓን ክርስቲያኖች በመጨረሻዎቹ ቀናት ይህን በጣም አስፈላጊ የሆነ ተልዕኮ በታማኝነት ሲያከናውኑ ቆይተዋል። በውጤቱም በአሁኑ ጊዜ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከጎናቸው ተሰልፈው ስለ ይሖዋ መንግሥት በመመስከር ላይ ይገኛሉ።

      19. ቅቡዓን ክርስቲያኖች ምን አገልግሎት የማከናወን መብት ያገኛሉ?

      19 ከዚህም በተጨማሪ የአምላክ እስራኤል አባላት በሌላ መንገድ ካህናት ሆኖ የማገልገል መብት ይጠብቃቸዋል። ምድራዊ ሕይወታቸው ካለፈ በኋላ ከሞት ተነስተው በሰማይ የማይጠፋ መንፈሳዊ ሕይወት ያገኛሉ። በዚያም በኢየሱስ መንግሥት ከእርሱ ጋር ገዥዎች ብቻ ሳይሆን የአምላክ ካህናትም ሆነው ያገለግላሉ። (ራእይ 5:​10፤ 20:​6) በምድር ላይ ያሉ ታማኝ የሰው ልጆች የኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት የሚያስገኛቸውን ጥቅሞች እንዲቋደሱ ያደርጋሉ። እነዚህ የአምላክ እስራኤል አባላት በራእይ መጽሐፍ 22ኛ ምዕራፍ ላይ ተመዝግቦ በሚገኘው የዮሐንስ ራእይ ላይም በድጋሚ “ዛፎች” ተብለው ተገልጸዋል። በራእዩ ላይ 144, 000ዎቹም “ዛፎች” በሰማይ “በየወሩ እያፈሩ አሥራ ሁለት ፍሬ” ሲሰጡ ታይተዋል። “የዛፎቹም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ [ናቸው]።” (ራእይ 22:​1, 2 NW ) ይህ እንዴት ያለ ድንቅ የክህነት አገልግሎት ነው!

  • በጽዮን ጽድቅ ይበቅላል
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • a አይሁዳውያን ያልሆኑ ሰዎች ከአይሁዳውያን ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱ ከመሆኑም በላይ ምድሪቱን መልሶ በመገንባቱ ሥራ እንደተባበሯቸው የሚታመን በመሆኑ ኢሳይያስ 61:​5 በጥንት ዘመንም ፍጻሜውን አግኝቶ ሊሆን ይችላል። (ዕዝራ 2:​43-58) ይሁን እንጂ ከቁጥር 6 አንስቶ ያለው ትንቢት የአምላክ እስራኤልን ብቻ የሚያመለክት ይመስላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ