-
‘አዲስ ስም’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
“እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታል”
9. በጽዮን ላይ የሚከሰተውን ለውጥ ግለጽ።
9 በምድራዊ ልጆቿ ለተወከለችው ሰማያዊቷ ጽዮን አዲስ ስም መሰጠቱ አስደሳች ለውጥ እንደሚጠብቃት የሚያሳይ ነው። ዘገባው እንዲህ ይላል:- “ከእንግዲህ ወዲህ:- የተተወች አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ:- ውድማ አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፣ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ:- ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም:- ባል ያገባች ትባላለች።” (ኢሳይያስ 62:4) ምድራዊቷ ጽዮን በ607 ከዘአበ ከጠፋችበት ጊዜ አንስቶ ውድማ ሆና ቆይታለች። ይሁን እንጂ ይሖዋ የተናገራቸው ቃላት ምድሪቱ ቀድሞ ወደነበረችበት ሁኔታ እንደምትመለስና ዳግመኛ በነዋሪዎች እንደምትሞላ የሚያረጋግጡ ናቸው። በአንድ ወቅት ጠፍታ የነበረችው ጽዮን ዳግመኛ የተተወችና ውድማ አትሆንም። በ537 ከዘአበ ኢየሩሳሌም ቀድሞ ወደነበረችበት ሁኔታ ስትመለስ ባድማ ሆና በቆየችባቸው ጊዜያት የነበረው ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ይለወጣል። ይሖዋ ጽዮን “ደስታዬ የሚኖርባት” ተብላ እንደምትጠራና ምድሯም “ባል ያገባች” እንደምትባል ገልጿል።—ኢሳይያስ 54:1, 5, 6፤ 66:8፤ ኤርምያስ 23:5 - 8፤ 30:17፤ ገላትያ 4:27-31
10. (ሀ) በአምላክ እስራኤል ላይ ለውጥ የተከሰተው እንዴት ነው? (ለ) የአምላክ እስራኤል “አገር” ምንድን ነው?
10 ከ1919 አንስቶ በአምላክ እስራኤል ላይ ተመሳሳይ የሆነ ለውጥ ተከስቷል። በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ወቅት ቅቡዓን ክርስቲያኖች አምላክ የተዋቸው ይመስሉ ነበር። ሆኖም በ1919 ቀደም ሲል በአምላክ ፊት የነበራቸውን ሞገስ መልሰው ከማግኘታቸውም በላይ የአምልኮ ሥርዓታቸውን ማጥራት ችለዋል። ይህም በትምህርቶቻቸው፣ በድርጅታቸውና በሥራቸው ላይ ለውጥ አስከትሏል። የአምላክ እስራኤል አባላት ወደ ‘አገራቸው’ ማለትም ወደ መንፈሳዊ ርስታቸው ወይም ወደ ሥራ መስካቸው ተመልሰዋል።—ኢሳይያስ 66:7, 8, 20-22
-
-
‘አዲስ ስም’የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
[በገጽ 339 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ይሖዋ ለሰማያዊቷ ጽዮን አዲስ ስም ይሰጣታል
-