የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘አዲስ ስም’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 13, 14. (ሀ) በጥንት ዘመን ኢየሩሳሌም ጥበቃ የምታስገኝ ከተማ የሆነችው እንዴት ነው? (ለ) በዘመናችን ጽዮን ‘በምድር ላይ ምስጋና’ የሆነችው እንዴት ነው?

      13 ይሖዋ ያወጣው አዲስ ምሳሌያዊ ስም ሕዝቡ ትምክህት እንዲያድርባቸው እንዲሁም እንደሚቀበላቸውና ባለቤታቸው እንደሆነ እንዲገነዘቡ ያደርጋል። ይሖዋ በመቀጠል አንድ ለየት ያለ ምሳሌ የተጠቀመ ሲሆን ሕዝቡን እንደተመሸገች ከተማ አድርጎ በመግለጽ እንዲህ አላቸው:- “ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ጉበኞችን በቅጥርሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንና ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምታሳስቡ፣ ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ።” (ኢሳይያስ 62:6, 7) ይሖዋ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ ታማኞቹ ቀሪዎች ከባቢሎን ከተመለሱ በኋላ ኢየሩሳሌም “በምድርም ላይ ምስጋና” ማለትም ለነዋሪዎቿ ጥበቃ የምታስገኝ የተመሸገች ከተማ ትሆናለች። በቅጥሮቿ ላይ የሚቆሙት ጉበኞች የከተማይቱን ደህንነት ለማስጠበቅና ለነዋሪዎቿ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ቀን ከሌት ነቅተው ይጠባበቃሉ።​—⁠ነህምያ 6:​15፤ 7:​3፤ ኢሳይያስ 52:​8

      14 በዘመናችን ይሖዋ ቅቡዓን ጉበኞቹን መሣሪያ አድርጎ በመጠቀም ከሐሰት ሃይማኖት ባርነት ነፃ መውጣት የሚቻልበትን መንገድ ቅን ለሆኑ ሰዎች አሳይቷል። እነዚህ ሰዎች ከመንፈሳዊ ብክለት፣ መጥፎ ከሆኑ ተጽዕኖዎችና ይሖዋን ከሚያሳዝኑ ድርጊቶች መራቅ ወደሚችሉበት ወደ ይሖዋ ድርጅት እንዲመጡ ግብዣ ሲቀርብላቸው ቆይቷል። (ኤርምያስ 33:​9፤ ሶፎንያስ 3:​19) እንዲህ ያለውን ጥበቃ ያገኙ ዘንድ ጉበኛው ማለትም መንፈሳዊውን ‘ምግብ በጊዜው’ የሚያቀርበው “ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚጫወተው ሚና ወሳኝ ነው። (ማቴዎስ 24:​45-47) ‘እጅግ ብዙ ሰዎችም’ ከጉበኛው ክፍል ጋር ተባብረው በመሥራት ጽዮን ‘በምድር ላይ ምስጋና’ እንድትሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።​—⁠ራእይ 7:​9

  • ‘አዲስ ስም’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 16. የይሖዋ አገልጋዮች ‘አምላክን ዕረፍት የማይሰጡት’ በምን መንገድ ነው?

      16 የይሖዋ አገልጋዮች ሳያቋርጡ እንዲጸልዩና የአምላክ ‘ፈቃድ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር እንድትሆን’ እንዲለምኑ ምክር ተሰጥቷቸዋል። (ማቴዎስ 6:​9, 10፤ 1 ተሰሎንቄ 5:​17) እውነተኛው አምልኮ ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ እንዲመለስ ያላቸው ፍላጎትና ተስፋ እስኪፈጸም ድረስ ‘ይሖዋን ዕረፍት እንዳይሰጡት’ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል። ኢየሱስ ተከታዮቹን ‘ቀን ከሌት ወደ አምላክ እንዲጮኹ’ አጥብቆ በማሳሰብ አዘውትሮ የመጸለይን አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ ገልጿል።​—⁠ሉቃስ 18:​1-8

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ