-
ይሖዋ ለራሱ የከበረ ስም ያደርጋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
11. (ሀ) ይሖዋ ‘የበቀል ቀን’ የሚያመጣው ለምንድን ነው? (ለ) ይሖዋ በጥንት ዘመን ‘የተቤዠው’ እነማንን ነው? በዘመናችንስ?
11 ይሖዋ ይህን ሥራ ራሱ የሚያከናውንበትን ምክንያት እንዲህ ሲል አክሎ ገልጿል:- “የምበቀልበት ቀን በልቤ ነውና፣ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና።” (ኢሳይያስ 63:4)b ሕዝቡን በሚያጠቁ ሰዎች ላይ የበቀል እርምጃ የመውሰድ መብት ያለው ይሖዋ ብቻ ነው። (ዘዳግም 32:35) በጥንት ዘመን ይሖዋ ‘የተቤዠው’ በባቢሎናውያን እጅ ወድቀው ብዙ መከራ ያሳለፉትን አይሁዳውያን ነበር። (ኢሳይያስ 35:10፤ 43:1፤ 48:20) በዘመናችን የተቤዠው ደግሞ ቅቡዓን ቀሪዎችን ነው። (ራእይ 12:17) እንደ ጥንቶቹ የአምላክ ሕዝቦች ቅቡዓን ቀሪዎችም ከሃይማኖታዊ ግዞት ነፃ ወጥተዋል። በተጨማሪም ልክ እንደ አይሁዳውያን ቅቡዓኑም ሆኑ ‘የሌሎች በጎች’ አባላት የሆኑ አጋሮቻቸው ስደትና ተቃውሞ ሲደርስባቸው ቆይቷል። (ዮሐንስ 10:16) በመሆኑም የኢሳይያስ ትንቢት በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖች አምላክ የወሰነው ጊዜ ሲደርስ እነሱን ለመታደግ ሲል እጁን ጣልቃ አስገብቶ እርምጃ እንደሚወስድ እርግጠኞች እንዲሆኑ ዋስትና ይሰጣቸዋል።
-
-
ይሖዋ ለራሱ የከበረ ስም ያደርጋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
b “የምቤዥበትም ዓመት” የሚለው አገላለጽ ይሖዋ ‘የሚበቀልበትን’ ጊዜ የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። በኢሳይያስ 34:8 ላይም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ መግለጫዎች እንዴት ጎን ለጎን እንደተሠራባቸው ተመልከት።
-