-
ይሖዋ ለራሱ የከበረ ስም ያደርጋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
14. ኢሳይያስ ምን ተገቢ የሆኑ ማሳሰቢያዎችን ሰጥቷል?
14 በቀድሞ ዘመን አይሁዳውያን ይሖዋ ለእነሱ ሲል ላደረጋቸው ነገሮች የነበራቸው አድናቆት የጠፋው ወዲያውኑ ነበር። በመሆኑም ኢሳይያስ ይሖዋ እነዚህን ነገሮች ያደረገላቸው ለምን እንደሆነ መለስ ብለው እንዲያስቡ ማድረጉ የተገባ ነው። ኢሳይያስ እንዲህ አለ:- “እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቸርነትና [“ፍቅራዊ ደግነት፣” NW ] የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም [“ፍቅራዊ ደግነቱ፣” NW ] ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን ትልቅ በጎነት አሳስባለሁ። እርሱም:- በእውነት ሕዝቤ፣ ሐሰትን የማያደርጉ ልጆች፣ ናቸው አለ፤ መድኃኒትም ሆነላቸው። በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፣ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፣ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።”—ኢሳይያስ 63:7-9
-
-
ይሖዋ ለራሱ የከበረ ስም ያደርጋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
17. (ሀ) ይሖዋ ለእስራኤላውያን ያለውን ፍቅር ያሳየው እንዴት ነው? (ለ) በዛሬው ጊዜ ምን ትምክህት ሊያድርብን ይችላል?
17 ያም ሆኖ መዝሙራዊው እስራኤላውያንን አስመልክቶ ሲናገር “ታላቅ ነገርንም በግብጽ . . . ያደረገውን ያዳናቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ” ብሏል። (መዝሙር 106:21) ዓመፀኝነታቸውና አንገተ ደንዳናነታቸው ብዙውን ጊዜ ለከፋ አደጋ ይዳርጋቸው ነበር። (ዘዳግም 9:6) ይሖዋ ለሕዝቡ ፍቅራዊ ደግነት ማሳየቱን አቁሞ ነበርን? በፍጹም፤ ከዚህ ይልቅ ኢሳይያስ እንደገለጸው “በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ።” ይሖዋ ምንኛ ርኅሩኅ ነው! ልክ እንደ ማንኛውም አፍቃሪ ወላጅ፣ አምላክ ልጆቹ ራሳቸው በፈጸሙት ስህተት ሳቢያም እንኳ መከራ ሲደርስባቸው በእጅጉ ያዝን ነበር። አስቀድሞ በተተነበየው መሠረት በተስፋይቱ ምድር ይመራቸው ዘንድ ‘የፊቱን መልአክ’ በመላክ ፍቅሩን ገልጾላቸዋል። ይህ መልአክ ሰው ሆኖ ወደ ምድር ከመምጣቱ በፊት በሰማይ ይኖር የነበረው ኢየሱስ መሆን አለበት። (ዘጸአት 23:20) በመሆኑም ይሖዋ “ሰው ልጁን እንዲሸከም” ሕዝቡን አንሥቶ ተሸክሟቸዋል። (ዘዳግም 1:31፤ መዝሙር 106:10) በተመሳሳይ ሁኔታ በዛሬው ጊዜም ይሖዋ የሚደርስብንን መከራ እንደሚያውቅና ከባድ ችግር በሚገጥመን ጊዜ እንደሚያዝንልን እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ‘ስለ እኛ የሚያስብ በመሆኑ የሚያስጨንቀንን ሁሉ በእርሱ ላይ መጣል’ እንችላለን።—1 ጴጥሮስ 5:7
-