-
ይሖዋ ለራሱ የከበረ ስም ያደርጋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
19, 20. አይሁዳውያን የሚያስታውሷቸው ነገሮች ምንድን ናቸው? ለምንስ?
19 አንዳንድ አይሁዳውያን መከራ እየተቀበሉ በነበረበት ወቅት ወደ ኋላ መለስ ብለው ቀደም ባሉት ዘመናት የተከናወኑትን ነገሮች አስበዋል። ኢሳይያስ እንዲህ አለ:- “እርሱም እንዲህ ብሎ የቀደመውን ዘመን አሰበ:- የበጎቹን እረኛ ከባሕሩ ያወጣው ወዴት ነው ያለ? ቅዱስ መንፈሱንም በመካከላቸው ያኖረ ወዴት ነው ያለ? የከበረውንም ክንድ በሙሴ ቀኝ ያስሄደ፣ ለራሱም የዘላለምን ስም ያደርግ ዘንድ ውኃውን በፊታቸው የከፈለ፣ በምድረ በዳም እንደሚያልፍ ፈረስ፣ በቀላይ ውስጥ ያለ ዕንቅፋት ያሳለፋቸው ወዴት ነው ያለ? ወደ ሸለቆ እንደሚወርዱ ከብቶች፣ እንዲሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዕረፍት አመጣቸው።”—ኢሳይያስ 63:11-14ሀ d
20 አዎን፣ አይሁዳውያን በአምላክ ላይ በማመፃቸው ምክንያት የደረሰባቸው መከራ ይሖዋ ጠላታቸው ሳይሆን አዳኛቸው የነበረባቸውን ጊዜያት መልሰው ለማግኘት እንዲመኙ አድርጓቸዋል። ‘እረኞቻቸው’ የነበሩት ሙሴና አሮን ቀይ ባሕርን ያላንዳች ችግር እንዴት እንዳሻገሯቸው ያስታውሳሉ። (መዝሙር 77:20፤ ኢሳይያስ 51:10) የአምላክን መንፈስ ከማሳዘን ይልቅ በሙሴና በሌሎች በይሖዋ የተሾሙ ሽማግሌዎች በኩል የመንፈሱን አመራር ያገኙበትን ጊዜ ያስታውሳሉ። (ዘኍልቁ 11:16, 17) ከዚህም በተጨማሪ ይሖዋ እነሱን ለመርዳት ሲል በሙሴ በኩል ‘የከበረውን ብርቱ ክንዱን’ የተጠቀመባቸው ጊዜያትም ትዝ ይሏቸዋል። ውሎ አድሮ አምላክ ከታላቁና እጅግ ከሚያስፈራው ምድረ በዳ አውጥቶ የዕረፍት ቦታ ወደሆነችውና ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ምድር ወስዷቸዋል። (ዘዳግም 1:19፤ ኢያሱ 5:6፤ 22:4) አሁን ግን እስራኤላውያን ከአምላክ ጋር የነበራቸውን ጥሩ ዝምድና በማጣታቸው ለመከራ ተዳርገዋል።
-
-
ይሖዋ ለራሱ የከበረ ስም ያደርጋልየኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
-
-
d ‘እርሱም የቀደመውን ዘመን አሰበ’ የሚለው አገላለጽ የቀድሞውን ዘመን ያሰበው ይሖዋ እንደሆነ ያመለክታል ብሎ መደምደም አይቻልም። ቀጥሎ የሰፈሩት ቃላት የይሖዋን ሳይሆን የአምላክን ሕዝብ ስሜት የሚገልጹ ናቸው። በመሆኑም ሶንሲኖ ቡክስ ኦቭ ዘ ባይብል ይህን አገላለጽ “ሕዝቡም የቀደመውን ዘመን አሰቡ” ሲል ተርጉሞታል።
-