የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘በፈጠርሁት ለዘላለም ደስ ይበላችሁ’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • 7, 8. ዓመፀኛ የሆኑት የይሖዋ ሕዝቦች አምላክን ያስቆጡት በምን መንገዶች ነው?

      7 ዓመፀኛ የሆኑት አይሁዳውያን ወራዳ በሆነው ምግባራቸው ይሖዋን በተደጋጋሚ ጊዜያት አስቆጥተውታል። ይሖዋ ጸያፍ ድርጊቶቻቸውን እንዲህ ሲል ገለጸ:- “ይህ ሕዝብ ዘወትር [“በፊቴ፣” አ.መ.ት ] የሚያስቈጡኝ ናቸው፤ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ በጡብም ላይ የሚያጥኑ፣ በመቃብርም መካከል የሚቀመጡ፣ በስውርም ስፍራ የሚያድሩ፣ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። የረከሰው መረቅ በዕቃቸው ውስጥ አለ። እነርሱም:- ለራስህ ቁም፣ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና ወደ እኔ አትቅረብ ይላሉ፤ እነዚህ በአፍንጫዬ ዘንድ ጢስ ቀኑንም ሁሉ የምትነድድ እሳት ናቸው።” (ኢሳይያስ 65:3-5) እነዚህ ጻድቅ መስለው የሚታዩ ሰዎች ይሖዋን ‘በፊቱ’ ያስቆጡት ሲሆን ይህም አጉል ድፍረትንና ንቀትን ሊያመለክት ይችላል። ጸያፍ የሆኑ ድርጊቶቻቸውን ለመደበቅ ምንም ያደረጉት ጥረት የለም። እጅግ ሊከበርና ሊፈራ በሚገባው አምላክ ፊት ኃጢአት መፈጸም ትልቅ ጥፋት አይደለምን?

      8 እነዚህ ራሳቸውን የሚያመጻድቁ ኃጢአተኞች ሌሎች አይሁዳውያንን ‘ከእናንተ ይበልጥ ቅዱስ ስለሆንን አትቅረቡን’ ይሉ ነበር። እንዴት ያለ ግብዝነት ነው! እነዚህ ‘ጻድቅ ነን ባዮች’ የአምላክን ሕግ በመጻረር ለሐሰት አማልክት መሥዋዕት ያቀርቡ የነበረ ከመሆኑም በላይ ዕጣን ያጥኑ ነበር። (ዘጸአት 20:​2-6) በመቃብር መካከል የሚቀመጡ ሲሆን ይህ ደግሞ በሙሴ ሕግ መሠረት የሚያረክስ ነበር። (ዘኍልቁ 19:​14-16) ከዚህም በተጨማሪ ርኩስ የሆነውን የእሪያ ሥጋ ይበላሉ።a (ዘሌዋውያን 11:​7) ሆኖም እንዲህ ያሉትን ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች በመፈጸማቸው ከሌሎቹ አይሁዶች ይበልጥ ቅዱስ እንደሆኑ አድርገው ያስቡ የነበረ ሲሆን ሌሎች ሰዎች ከእነርሱ ጋር በመቀራረብ ብቻ ይቀደሱ ወይም ይነጹ ይመስል አጠገባቸው እንዳይደርሱ ይከለክሏቸው ነበር። ይሁንና “ለእሱ ብቻ የተወሰነ አምልኮ” [NW ] እንዲቀርብለት የሚፈልገው ይሖዋ ያለው አመለካከት ከዚህ ፈጽሞ የተለየ ነው!​—⁠ዘዳግም 4:​24

  • ‘በፈጠርሁት ለዘላለም ደስ ይበላችሁ’
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 2
    • a ብዙዎች እነዚህ ኃጢአተኞች በመቃብር ሥፍራዎች ይቀመጡ የነበረው ከሙታን ጋር ለመገናኘት ሲሉ እንደነበረ ያምናሉ። የእሪያ ሥጋ መብላታቸው ደግሞ ከጣዖት አምልኮ ጋር ዝምድና ሊኖረው ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ